ደደቢት የአፍሪካ ፈተናውን እሁድ ይጀምራል

የ2005 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮኑ ደደቢት በቅድመ ማጣርያው የዛንዚባሩን ኬኤምኬኤምን እሁድ በ10 ሰአት በአዲስ አበባ ስታዲየም ያስተናግዳል፡፡

ከ40 ቀናት በላይ በእረፍት ላይ የቆየው የአሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ ቡድን ከዛንዚባር የእግርኳስ ደረጃ እና የክለቦች አንፃር በጨዋው ከባድ ፈተና ይገጥመዋል ተብሎ አይታሰብም፡፡

አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ በቡድኑ ውስጥ ምንም የተጫዋቾች ጉዳት እንደሌለ እና ሁሉም በጥሩ አቋም ላይ እንደሚገኙ ገልፀው በውድድሩ እስከምድብ ድልድሉ የመጓዝ አላማ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

የዛንዚባሩ ሻምፕዮን ረቡእ አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን ትላንት በአአ ስታዲየም ልምምድ አድርገዋል፡፡ ኬኤምኬኤም የ2013 የዛንዚባር ሊግን ያሸነፈ ሲሆን ደደቢት አምና ክብሩን በ61 ነጥቦች ማሳካቱ ይታወሳል፡፡

ጠቃሚ ነጥቦች

-አምና በተመሳሳይ ወቅት ቅዱስ ጊዮርጊስ በቅድመ ማጣርያው ሌላውን የዛንዚባር ክለብ ጃምሁሪን በደርሶ መልስ ውጤት 8-0 አሸንፏል፡፡

-ደደቢት በቻምፒዮንስ ሊግ ሲካፈል ዘንድሮ ለመጀመርያ ጊዜ ነው፡፡ ሰማያዊው ጦር ለ2 ጊዜያት ያህል በኮንፌድሬሽን ዋንጫ ተሳትፈዋል፡፡

-ደደቢት እሁድ ካሸነፈ ከ6 ተከታታይ ግጥሚያዎች በኃላ የመጀመርያው ይሆናል፡፡ ቡድኑ ባለፉት 3 የሊግ እና 3 የሲቲ ካፕ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም፡፡

-የቀድሞው የመከላከያ እና የንግድ ባንክ አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ ለመጀመርያ ጊዜ በአፍሪካ ውድድር ላይ በአሰልጣኝነት ይቀርባሉ፡፡

{jcomments on}