የኢትዮጵያ ዋንጫ ፡ ሲዳማ ቡና እና አርባምንጭ ከነማ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ

 

የ2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዋንጫ (ጥሎ ማለፍ) ትላንት በተደረጉ የመጀመርያ ዙር ጨዋታዎች ተጀምሯል፡፡

በ8፡00 አርባምንጭ ከነማ ከ ሙገር ባደረጉት ጨዋታ አርባምንጭ ከነማ በመለያ ምቶች በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል፡፡ ሙገር ሲሚንቶ ኤፍሬም ቀሬ በ17ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ 1-0 ሲመራ ቢቆይም ታገል አበበ በ65ኛው ደቂቃ ግብ አስቆጥሮ አርባምንጭ ከነማን አቻ አድርጓል፡፡ የጨዋታው መደበኛ ክፍለ ጊዜም 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡ አሸናፊውን ለመለየት በተሰጡት የመለያ ምቶች አርባምንጭ ከነማ 4-3 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን አረጋግጧል፡፡

በ10፡00 ሲዳማ ቡና ወልድያን በቀላሉ 3-0 አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል፡፡ አንዱአለም ንጉሴ ደምቆ በዋለበት ጨዋታ በ36ኛው ፣ በ73ኛው እና 81ኛው ደቂቃ ላይ 3 ግቦችን አስቆጥሮ ሐት-ትሪክ ሰርቶ ወጥቷል፡፡ አንዱአለም ንጉሴ በዙህ የውድድር ዘመን ወልድያ ላይ ሐት-ትሪክ የሰራ ተጫዋች ሆኗል፡፡ ከአንድ ሳምንት በፊት በሊጉ ቢንያም አሰፋ ወልድያ ላይ 3 ግቦች ማስቆጠሩ ይታወሳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *