የኢትዮጵያ ከ23 አመት በታች (ኦሎምፒክ) ብሄራዊ ቡድን በኮንጎ ብራዛቪል ለሚደረገው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ውድድር ለማለፍ የመጀመርያ የማጣርያ ጨዋታውን ከሱዳን አቻው ጋር በመጪው እሁድ ያከናውናል፡፡
አዲስ አበባ ስታድየም ለአፍሪካ ወጣቶች የአትሌቲክስ ቻምፒዮና ውድድር በመያዙ ጨዋታው የሚከናወነው በድሬዳዋ ስታድየም ሲሆን ተጋጣሚው የሱዳን ብሄራዊ ቡድን ብሄራዊ ቡድን ትላንት አዲስ አበባ መድረሱም ታውቋል፡፡
ብሄራዊ ቡድኑ ከ15 ቀናት በፊት 43 ተጫዋቾችን በመምረጥ ዝግጅት እያደረገ ሲሆን ተጫዋቾቹን ወደ 20 ቀንሶ ወደ ድሬዳዋ አቅንቷል፡፡
ጨዋታውን 4 ኬንያውያን ዳኞች እና ጅቡቲያዊ ኮሚሽነር ይመሩታል፡፡
ማርያኖ ባሬቶ የመረጧቸው የመጨረሻዎቹ ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው፡-
ተ.ቁ | ስም | የሚጫወትበት ቦታ |
---|---|---|
1 | አሰግድ አክሊሉ | ግብ ጠባቂ |
2 | ክብረአብ ዳዊት | ግብ ጠባቂ |
3 | ሳላዲን በርጊቾ | ተከላካይ |
4 | ዘካርያስ ቱጂ | ተከላካይ |
5 | አንዳርጋቸው ይላቅ | ተከላካይ |
6 | አወት ገ/ሚካኤል | ተከላካይ |
7 | አህመድ ረሺድ | ተከላካይ |
8 | ቴዎድሮስ በቀለ | ተከላካይ |
9 | ምንተስኖት አዳነ | አማካይ |
10 | ናትናኤል ዘለቀ | አማካይ |
11 | ሱራፌል ጌታቸው | አማካይ |
12 | ጋቶች ፓኖም | አማካይ |
13 | ሚካኤል በየነ | አማካይ |
14 | እንዳለ ከበደ | አማካይ |
15 | ሀይደር ሸሪፍ | አማካይ |
16 | ዳዋ ሁቴሳ | አጥቂ |
17 | ራምኬል ሎክ | አጥቂ |
18 | ምንይሉ ወንድሙ | አጥቂ |
19 | አብዱራህማን ሙባረክ | አጥቂ |
20 | ኤፍሬም ቀሬ | አጥቂ |