ኤልያስ ማሞ እና ጋቶች ፓኖም ስለ ደርቢው ይናገራሉ

ኢትዮጵያ ቡና በ8ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የከተማ ተቀናቃኙ ቅዱስ ጊዮርጊስን በአዲስ አበባ ስታድየም ዕሁድ በ10፡00 ያስተናግዳል፡፡ አደገኞቹ ቃሊቲ በሚገኘው የኒያላ ሜዳ ልምምዳቸውን ሲያደርጉ የተገኘችው ሶከር ኢትዮጵያ የቡድኑን 2ኛ አምበል ጋቶች ፓኖም እና አማካዩን ኤልያስ ማሞን ስለጨዋታው እና ተያያዥ ጉዳዮች አናግራለች፡፡

“የደርቢ ጨዋታ ከባድ ነው” ጋቶች ፓኖም

ስለዝግጅት

“ዝጅግት ጥሩ ነበር፡፡ ሰኞ ጠንካራ ልምምድ ሰርተናል፡፡ ማክሰኞ ዕለት ደግሞ አርፈን ነበር፡፡ ልምምድ በጣም ጥሩ ነው፡፡ ለጨዋታው ተዘጋጅተናል፡፡”

የግብ ማግባት ችግር

“ግብ ለማግባት በተቻለን አቅም ተዘጋጅተናል፡፡ ግብ ካገባህ ሁሉም ነገር ይስተካከላል ስለዚህም በዚህ ላይ ትኩረት ሰጥተን ልምምድ ስንሰራ ነበር፡፡”

ስለሸገር ደርቢ

“የደርቢ ጨዋታ እንደሚታወቀው ከባድ ነው፡፡ የነጥብ ልዩነት ቢኖርም ከባድ ነው፡፡ እኛም ተዘጋጅተናል፡፡ እኛ ለሌላ ነገር ሳይሆን ለማሸነፍ ነው የምንጫወተው፡፡ ምክንያቱም የነጥብ ልዩነቱን ለማጥበብ ግዴታ ለማሸነፍ ነው የምንጫወተው፡፡ እኔ በበኩሌ ለክለቡ የተሻለ እና ጥሩ እንቅስቃሴ ለማድረግ ነው ዕቅዴ፡፡ ለክለቡ ጥሩ ውጤት ለማምጣት መጣር ነው ፍላጎቴ፡፡”

“ጨዋታው ለኛ ከምንምግዜም በላይ ወሳኝ ነው” ኤልያስ ማሞ

ስለዝግጅት

“ዝግጅት በጣም ጥሩ ነው፡ በጥሩ መንፈስ ልምምድ እያደረግን ነበር፡፡ አራት ቀን ሆኖናል፡፡ ከፊት ላለው ትልቅ ጨዋታ በጥሩ መልኩ ተዘጋጅተናል፡፡”

ስለሸገር ደርቢ

“አሁን ያለን ጨዋታ ትልቅ ጨዋታ ነው፡፡ የከተማው ደርቢ ነው፡፡ ከዚህ በፊትም ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆኜ አሁን ደግሞ በቡና ማልያ በደርቢው ላይ ተጫውቻለው፡፡ አሁን ከፊታችን ያለው ጨዋታ ለእኛ ከምንግዜም በላይ ወሳኝ ነው፡፡ ሶስት ነጥቡ በጣም ነው የሚያስፈልገን፡፡ ከሚገባው በላይ ዝግጅት አድርገናል፡፡”

ስለግብ ማስቆጠር ችግር

“እንደተመለከትነው ሰባቱ ጨዋታዎች ላይ ብዙ የግብ ማግባት እድሎችን እናባክናለን፡፡ እዚህ ላይ እየሰራን ነው፡፡ አሁን ላለን ጨዋታም ችግሩን ለመቅረፍ ጠንክረን እየሰራን ነው፡፡ በጨዋታው ግቦችን አስቆጥረን አሸንፈን እንወጣለን ብዬ አስባለው፡፡”

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *