ኮንፌዴሬሽንስ ካፕ፡ ደደቢት ነገ ወደ ሌጎስ ይበራል

በአፍሪካ ኮንፌድሬሽንስ ካፕ አንደኛ ዙር ጨዋታ በመጪው ቅዳሜ ከናይጄርያው ዎሪ ዎልቭስ ጋር የሚጫወተው ደደቢት በነገው እለት ወደ ስፍራው ያመራል፡፡

ደደቢት ኮት ዲ ኦርን በድምር ውጤት 5-2 አሸንፈው ካለፉ በኋላ ለቀጣዩ ዙር ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በጨዋታው ባህርዳር ላይ ግብ ያስቆጠረው ስዩም ተስፋዬ ፣ በመልሱ ጨዋታ የተጎዳው ሳምሶን ጥላሁን እና ተከላካዩ አክሊሉ አየነው ጉዳት ላይ በመሆናቸው ከቡድኑ ጋር ወደ ናይጄርያ የማይጓዙ ሲሆን ከኮት ዲ ኦር ጋር በተደረገው ጨዋታ ቀይ ካርድ የተመለከተው ጋናዊው ተከላካይ አዳሙ ሞሃመድ ደግሞ በቅጣት ምክንያት አይጓዝም፡፡ በአንፃሩ ለረጅም ሳምንታት በጉዳት ከሜዳ ርቆ የሰነበተው ያሬድ ዝናቡ ከጉዳቱ አገግሟል፡፡

የናይጄርያው ዋሪ ዎልቭስ በሌጎስ የሚገኝ ክለብ ሲሆን ከዚህ በፊት በኮንፌድሬሽንስ ካፕ ለ3 ጊዜያት ተካፍሏል፡፡

በሁለቱ ክለቦች የሚካሄደው የመጀመርያ ጨዋታ በመጪው ቅዳሜ ማርች 14/2015 አመሻሽ 11፡30 የሚካሄድ ሲሆን የመልሱ ደግሞ ኤፕሪል 5 በባህርዳር ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *