‹‹ የኢትዮጵያ ቡና እና ፉልሃም ጨዋታ ገና አልተረጋገጠም… ››

ኢትዮጵያ ቡና ከእንግሊዙ የቻምፕዮን ሺፕ ክለብ ጋር በጁላይ ወር የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋል ተብሎ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ቢዘገብም ጨዋታው መደረጉ እንዳልተረጋገጠ ከክለቡ የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የማርኬቲንግ ዴፓርትመንት ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፁት ጨዋታውን እንደሚያካሄዱ ባያረጋግጡም ጥረቶች እየተደረጉ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

‹‹ ክለባችን ከፉልሃም ጋር የሚደረገውን የወዳጅነት ጨዋታ እውን ለማድረግ በኤጀንቶች በኩል ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ ጥረታችን ከተሳካ ምእራብ ለንደኑ ክለብ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ እናደርጋለን፡፡ በመጀመርያ ለመጫወት ያቀድነው ከክለቡ የወጣቶች አካዳሚ ጋር ሲሆን በመቀጠል ከዋናው ቡድን ጋር እንጫወታለን ›› ሲሉ አቶ ሙሉጌታ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *