የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ሰርቢያዊው ሰርድዮቪች ሚሉቲን ‹‹ ሚቾ ›› የሱዳኑን ክለብ አል-ሂላል ለማሰልጠን በይፋ ተስማምተዋል፡፡ በክረምቱ የዝውውር መስኮት የኦምዱርማኑን ታላቅ ክለብ ከተቀላቀለው አበባው ቡታቆ ጋርም በድጋሚ ተገናኝተዋል፡፡
ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በቆዩባቸው 5 የውድድር ዘመናት በሙሉ ከክለቡ ጋር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ያነሱት ሰርቢያዊው ታክቲሽያን ለሁለተኛ ጊዜ በተመለሱበት አል-ሂላል ከዚህ ቀደም ያሳኩትን የአፍሪካ ውድድር ስኬት እንደሚደግሙ ይጠበቃል፡፡
ለአበባው ከፍተኛ ደረጃ መድረስ የሚቾ አስተዋፅኦ ጎልቶ የሚጠቀስ ሲሆን በ1998 ቅዱስ ጊዮርጊስ የግብፁ ኢ.ኤን.ፒ.ፒ.አይን በደርሶ መልስ 1-0 አሸንፎ ወደ ተከታዩ ዙር ሲያልፍ ለአበባው በአፍሪካ ውድድር ለመጀመርያ ጊዜ የመሰለፍ እድል የሰጡትም ሰርቢያዊው ነበሩ፡፡
ፎቶ – አበባው እና ሚቾ በቅዱስ ጊዮርጊስ