ኮንፌድሬሽን ካፕ፡ “ለጨዋታው ተዘጋጅተናል” ጋብርኤል አህመድ

የደደቢቱ ጋናዊ አማካይ ጋብርኤል አህመድ ክለቡ ዛሬ ከናይጄሪያው ዋሪ ዎልቭስ ጋር ላለበት ወሳኝ የካፍ ኮንፌድሬሽን ካፕ በቂ ዝግጅት እንዳደረጉ ለሶከር ኢትዮጵያ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

በአብዛኛው የእግርኳስ አፍቃሪ ሻይቡ በሚለው የቅፅል ስሙ የሚታወቀው ጋብርኤል ስለ ደደቢት ዝግጅት እንዲህ ብሏል፡፡

“ጠንካራ ልምምድ ሰርተናል፡፡ ልምምዳችን ጥሩ ነበር፡፡ የአየር ፀባዩ አመቺ ባይሆንም ለጨዋታው ተዘጋጅተናል፡፡”

ጋናዊው ደደቢት ከናይጄርያ ጥሩ ውጤት ይዘው የመመለስ አላማ እንዳላቸውም ተናግሯል፡፡ “ዋሪ ላይ ጥሩ ውጤት ይዘን ጨዋታውን ባህርዳር ላይ ለመጨረስ ነው ፍላጎታችን፡፡ ነገር ግን እነሱ ልምድ ያላቸው ስለሆኑ መጠንቀቅ ይኖርብናል፡፡

“የአጨራረስ ችግር አለብን ነገር ግን ነገሮች መልካም ይሆናሉ ብዬ አስባለው፡፡ በጨዋታው ያለብንን የተከላካይ እጥረት ለመቅረፍ እኔ በመሃል ተከላካይነት ጨዋታውን እጀመራለው፡፡ ከአስቻለው ታመነ ጋር እጣመራለሁ ብዬ አስባለሁ፡፡ ›› ሲል አስተያየቱን ቋጭቷል፡፡

ዋሪ ዎልቭስ ደደቢትን 11፡30 ላይ የሚያስተናግድ ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *