ሉሲዎቹ ነገ ወደ ካሜሮን ያቀናሉ

ኮንጎ ብራዛቪል ለምታዘጋጀው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ማጣሪያ ከካሜሮን አቻው ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ነገ ለመልሱ ጨዋታ ወደ ያውንዴ ያቀናል፡፡ በአሰልጣኝ በኃይሏ ዘለቀ የሚመራው ብሄራዊ ቡድኑ በመጀመሪው ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡ ብሄራዊ ብድኑ ጠንካራ ዝግጅት ሲሰራ ቆይቷል፡፡ አሰልጣኟ እና ተጫዋቾቹ ካሜሮንን በሜዳዋ ላይ በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ የሚችሉበትን ውጤት ማስመዝገብ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡ ሉሲዎች ነገ 18 ተጫዋቾችን ይዘው ወደ ካሜሮን እንደሚጓዙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *