የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ አሰልጣኝ ጥላሁን መንገሻን አሰናበተ፡፡ ባሰለፍነው ክረምት ቡድቡን የተረከበው ጥላሁን በቅርብ ጊዜያት የተመዘገበው ውጤት ተንተርሶ ክለቡ እንዳሰናበታቸው ተነግሯል፡፡ በተለይ ቡና ከዳሽን ቢራ ጋር ያለምንም ግብ አቻ መለያየቱ እንዲሁም በአርባምንጭ ከነማ መሸነፉ በደጋፊው እና በክለቡ አመራሮች ላይ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሶ ነበር፡፡ አሰልጣኝ ጥላሁን የቆይታ ግዜም አጠራጣሪ ነበር፡፡ ዛሬ ጠዋት ክለቡ አሰልጣኙ ከስራ ገበታው እንዲነሳ አድርጓል፡፡ በምትኩም ምክትል አሰልጣኝ ሆኖ ሲያገለግል ነበረው አንዋር ያሲን ቡድኑን በዋና አሰልጣኝነት የሚመራ ይሆናል፡፡ አንዋር መጀመሪው ጨዋታውን በሸገር ደርቢ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያደርጋል፡፡