ዳሽን ቢራ የክለቡ ዋና አሰልጣኝ የሆነው ሳምሶን አየለን ከኃላፊነት ማንሳቱን አስታውቋል፡፡ ዛሬ ጠዋት በተደረገው የቦርድ ስብሰባ አሰልጣኙ የሚጠበቅባቸውን ውጤት ማስመዝገብ ባለመቻላቸው ከኃላፊነታቸው ለማንሳት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
በክረምቱ የዝግጅት ወቅት ዳሽን ቢራን በከፍተኛ የፊርማ ክፍያ የተረከቡት የቀድሞው የሐረር ሲቲ አሰልጣኝ በከፍተኛ የፊርማ ክፍያ የተገዙ ተጫዋቾችን ያሰባሰበ ከፍተኛ ልምድ ያለው ስብስብ ቢይዙም ቡድኑን በወራጅ ቀጠና እንዲገኝ ማድረጋቸው ከደጋፊው ከፍተኛ ተቃውሞ እንዲነሳባቸው አድርጓል ተብሏል፡፡
የዳሽን ዋና አሰልጣኝነት ቦታን ምክትሉ ካሊድ መሃመድ የሚይዙት ሲሆን አሰልጣኙ ባለፈው የውድድር ዘመን አሰልጣኝ መኮንን ከተሰናበቱ በኋላ በጊዜያዊ አሰልጣኝነት የውድድር ዘመኑን ማጠናቀቃቸው ይታወሳል፡፡
ፎቶ – Dashen Beer FC.