የሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ የሆነውን አቤል ያለው የጉዳት ሁኔታ በተመለከተ የተገኘ አዲስ መረጃ እነሆ !

ሲዳማ ቡና ከተከታታይ አራት ጨዋታዎች ነጥብ መጣል በኋላ ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም አርባምንጭ ከተማን ሦስት ለዜሮ በማሸነፍ ወደ ድል ተመልሰዋል።
በጨዋታው የመጀመርያ አጋማሽ ላይ የሊጉን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነትን በ14 ጎሎች እየመራ የሚገኘው አቤል ያለው ጉዳት አስተናግዶ ለተሻለ ህክምና ወደ ቤተዛታ ሆስፒታል ማምራቱን ዘግበንላችሁ ነበር። አሁን የክለቡ ፊዚዮቴራፒስት ብሩክ ደበበ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለው ከሆነ “X-ray ተነስቷል ሆኖም የተሰጋውን ያህል ከባድ አይደለም። ኤክስሬው የሚያሳየው ውጤት ጥሩ ነው። በቀጣይ ቀናቶች የህክምና ሂደቱን በመከታተል አቤል በፍጥነት ወደ ሜዳ እንዲመለስ ከፍተኛ ሥራዎችን እንሰራለን ብለዋል።”
አቤል ጉዳቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ወሳኝ ጨዋታ ሊያመልጠው እንደሚችል ሰምተናል።

