“የተፈራውን ያህል አይደለም።” ቅዱስ ቂርቆስ

“የተፈራውን ያህል አይደለም።” ቅዱስ ቂርቆስ

👉 “እንደ ሰጋሁት የተፈራውን ያህል አይደለም።”

👉 “እግዚአብሔር ይመስገን በጣም ደህና ነኝ።”

በቅርቡ ብዙዎችን ያሳዘነ ጉዳት ካስተናገደው ወጣቱ የመስመር አጥቂ ቅዱስ ቂርቆስ ጋር የተደረገ ቆይታ !

ባሳለፍነው 33ኛው ሳምንት ወላይታ ድቻ ከ ኢትዮጵያ መድን ጋር ባደረጉት ጨዋታ በመጨረሻው ደቂቃ ላይ ተቀይሮ የገባው የመስመር አጥቂው ቅዱስ ቂርቆስ ላይ ብዙዎችን በእንባ ያራጨ ጉዳት ማስተናገዱ ይታወሳል። በፍጥነት ለተሻለ ሕክምና ወደ ቤተ ዛታ ሆስፒታል ያመራው ተጫዋቹ የመጀመርያ ሕክምና ካደረገ በኋላ ማምሻውን ወደ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ሕክምናውን ለመከታተል ያቀና ሲሆን የቁርጭምጭሚት ውልቃትና የተወሰነ የአጥንት መሰንጠቅ ጉዳት እንደረሰበት ታውቋል።

ተጫዋቹ ቅዱስ ቂርቆስ ከትናንት በስቲያ በሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል የተሳካ የቀዶ ጥገና ሕክምና አድርጎ ትናንት በሰላም ወደ ቤቱ መግባቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ይህን ተከትሎ ሶከር ኢትዮጵያ ከቅዱስ ጋር ዛሬ ረፋድ ላይ በስልክ በነበረው ሁኔታ ዙርያ ጋር አጭር ቆይታ አድርጋለች።

“ይህ ይሆናል ብዬ አላሰብኩም በሆነው ነገር በጣም ደንግጬ ነበር ሆኖም እግዚአብሔር ይመስገን በጣም ደህና ነኝ። የተሰጋውን፣ የተፈራውን ያህል አይደለም። ብዙም አሳሳቢ አይደለም። ጥሩ ሕክምና አድርጌአለሁ። በቀጣይ ሀኪሞቹ ቀጠሮ ሰጥተውኛል እሄዳለሁ። በቅርቡም ከፈጣሪ ጋር ወደ ሜዳ እመለሳለው።” ብሎ በመጨረሻም “ጉዳት ካስተናገደኩበት ጊዜ ጀምሮ ከጎኔ ለነበሩት ላዘኑልኝ ለቡድን አጋሮቼ ፣ አሰልጣኞቼ ፣ የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች እንዲሁም የወላይታ ዞን አስተዳደር አመራሮችን እና መላው የስፖርት ቤተሰቦች በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ እግዚአብሔር ያክብርልኝ በማለት ምስጋናውን አቅርቧል።”