አርባምንጭ ከተማ የናይጄሪያዊውን ተከላካይ ውል አድሷል

በከፍተኛ ሊጉ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር የነበረው ናይጄሪያዊው ተከላካይ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ውሉ ተራዝሞለታል፡፡

በአሠልጣኝ መሳይ ተፈሪ መሪነት በአርባምንጭ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እየሰሩ የሚገኙት አዞዎቹ የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታቸውን የፊታችን ዕሁድ ሶዶ ላይ ከወላይታ ድቻ ጋር ለማድረግ ቀጠሮ ይዘዋል፡፡ ከቀናቶች በፊት ሁለት የኬኒያ ዜግነት ያላቸውን ተጫዋቾች ወደ ክለቡ የቀላቀለው ክለቡም የናይጄሪያዊውን የመሐል ተከላካይ ማርቲን ኦቼናን ኮንትራት አራዝሟል።

የሀገሩን ክለብ ሪቨር ዩናይትድን ለቆ በተጠናቀቀው የውድድር አመት ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋላ በከፍተኛ ሊጉ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ቆይታን ያደረገው ይህ ተከላካይ ክለቡ ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲመለስ ከረዱ ተጫዋች መሐከል አንዱ መሆኑን ተከትሎ ክለቡ ለተጨማሪ አንድ አመት እንዲቀጥል አድርጓል። ይህንን ተከትሎም በክለቡ ውስጥ የሦስት የውጪ ዜጋ ተጫዋቾችን ኮታ ተይዟል፡፡