የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ወሳኝ ጨዋታዎች – ከሁሉም ቦታ በቀጥታ..

 FT  መቀለ ከተማ  1-1  ወልዋሎ አዩ. 

64′ አስራት ሸገሬ | 90+3′ አለምአንተ ካሳ


ተጠናቀቀ!

ጨዋታው 1-1 ተጠናቋል፡፡ ወልዋሎ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማደጉን አረጋግጧል፡፡ መቀለ ከተማ ከምድብ ለ 2ኛ ጋር ወደ ፕሪምየር ሊግ ለማለፍ ድሬዳዋ ላይ የሚጫወት ይሆናል፡፡

ጎልልል!!

አለምአንተ ካሳ ወልዋሎን አቻ አድርጓል፡፡

ጎልልል! መቀለ!!!

አስራት ሸገሬ ባለሜዳዎቹን ቀዳሚ አድርጓል፡፡

46′ ሁለተኛው አጋማሽ ተጀመረ!

የመጀመርያው አጋማሽ ያለ ግብ ተጠናቋል፡፡

30′ የወልዋሎ ተጫዋቾች ኳስ ከግብ ክልል ውጪ አክርረው በመምታት የመቀለውን ግብጠባቂ እየፈተሹ ይገኛሉ፡፡

ሌላ የሚያስቆጭ አጋጣሚ!
21′
የመቀለው አጥቂ ያሬድ ከበደ መቀሌዎች በፈጣን መልሶ ማጥቃት ያገኙትን ኳስ ሳይጠቀምበት ቀረ፡፡

የሚያስቆጭ አጋጣሚ!
18′
የወልዋሎው አጥቂ ቴዎድሮስ መንገሻ ከመሀል የተላከለትን ኳስ የመቀለውን ግብ ጠባቂ ምንተስኖት ይደጉን አልፎ ቢሞክርም ለጥቂት ወደ ውጪ ወጣበት፡፡

15′ በዝናብ ታጅቦ እየተካሄደ በሚገኘው በዚሁ ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች በፍጥነት ወደ ግብ በመድረስ ግብ ለመስቆጠር ጥረት እያደረጉ ነው፡፡

ተጀመረ!

ጨዋታው ተጀምሯል፡፡ አዲሱ የመቀለ አለምአቀፍ ስታዲየም በከፍተኛ ሁኔታ በሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች ተሟልቷል፡፡

– ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት መጠነኛ ዝናብ በስታዲየሙ ቢጥልም የሁለቱም ክለቦች ደጋፊዎች እጅግ ደማቅ የሆነ ድጋፍን ለቡድናቸው እየሰጡ ይገኛል፡፡


 FT  ጅማ ከተማ  3-1  ወልቂጤ ከተማ 

36′ 48′ ኄኖክ መሀሪ 55′ አቅሌሲያስ ግርማ | 89′ አክሊሉ ተፈሪ


ተጠናቀቀ!

ጨዋታው በጅማ ከተማ 3-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ጅማ ከተማ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል፡፡ ሀዲያ ሆሳዕና ደግሞ ከመቀለ ከተማ ጋር ወደ ሊጉ ለማደግ የመለያ ጨዋታ ድሬዳዋ ላይ የሚያደርግ ይሆናል፡፡

89′ አክሊሉ ተፈሪ ለወልቂጤ ከተማ የመጀመርያ ግብ አስቆጥሯል፡፡

83′ ወልቂጤ ከተማዎች ጎሎች ከተቆጠሩባቸው በኃላ ሙሉ ለሙሉ ለማጥቃት ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።

67′ አቅሌሲያ ግርማ በግል ጥረቱ ከማህል ሜዳ ጀምሮ እየገፋ በመሄድ የሞከረው ኳስ ግብ ጠባቂው ለጥቂት አውትቶበታል።
66′ ተመስገን ገ/ኪዳን በሁለት ቢጫ ከሜዳው በቀይ ካርድ ወቷል።

ልልል!!!

55′ አቅሌሲያ ግርማ ከ ግብ ጠባቂው ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝቶ ግብ ጠባቂውን በማለፍ ጅማ ከተማ 3ለ0 እንዲመራ አድርጎታል።

ጎልልል!!!!

48′ ኄኖክ መሃሪ በረጅሙ የተጣለለትን ኳስ በሚገባ ተቆጣጥሮ የጅማን ሁለተኛ ጎል አስቆጠረ።

46′ ሁለኛው አጋማሽ ተጀመረ!

የመጀመርያው አጋማሽ ተጠናቋል፡፡

45+13′ ተመስገን ገብረኪዳን ከግብ ጠባቂው ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝቶ የጅማን መሪነት ሊያሰፋ የሚችልበትን እድል አምክኗል፡፡

45+11′ ከ18 ደቂቃዎች መቋረጥ በኋላ ጨዋታው ቀጥሏል፡፡

45+5′ እስካሁን ድረስ ጨዋታው ያልጀመረ ሲሆን የወልቂጤ ከተማ ተጫዋቾች ዳጋፊዎቻቸውን ለማረጋጋት ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

38′ ከጎሉ መቆጠር በኃላ የወልቂጤ ከተማ ደጋፊዎች ከፓሊስ ጋር በፈጠሩት ግብ ግብ ጨዋታው ተቋርጧል።

ጎልልል!!!! ጅማ!
36′ ሄኖክ መሃሪ ከማዕዘን የተሻገረውን ኳስ በግሩም ሁኔታ ጎል አስቆጠረ።

15′ እስካሁን ባለው የጨዋታ እንቅስቃሴ ወደ ጎል በመድረስ ረገድ ባለ ሜዳዎቹ ጅማ ከተማዎች የተሻሉ ቢሆኑም የጠራ የግብ ማግባት እድል ግን መፍጠር አልቻሉም። በተቃራኒው ወልቂጤዎች ተከላክለው በመልሶ ማጥቃት ለመጫወት እየጣሩ ይገኛሉ።

1′ ጨዋታው ተጀምሯል፡፡ 


 FT  ሀዲያ ሆሳዕና  0-0  ሀላባ ከተማ 

ተጠናቀቀ!

ጨዋታው ያለግብ ተጠናቀቀ!

ዘካርያስ ፍቅሬ ሀላባን አሸናፊ የሚያደርግ ግልፅ የጎል አመከነ፡፡ የሚያስቆጭ አጋጣሚ !
ተጨማሪ ደቂቃ – 3

85′ ሀላባዎች በጨዋታው የመጀመርያ ሙከራ በአቦነህ ገነቱ አማካኝነት ሞከረውን ግብ ጠባቂው አዳነው ።
78′ ያለፉትን 20 ደቂቃዎች ሀድያዎች በሁሉም ረገድ ከሀላባዎች ተሽለው ጫና ፈጥረው እያጠቁ ይገኛሉ ። 

73′ ሀድያዎች አሁንም በድጋሚ መሪ የሚሆኑበትን እድል የግቡ አግዳሚ መለሰባች ። አቢዮ ኤርሳሞ የሚገኘው ደጋፊ ድጋፉን እየሰጣቸው ይገኛል 
68′ ሁለቱም ቡድኖች ከወዲሁ ሦስት ተጨዋቾቻቸውን ቀይረው አጠናቀዋል። 


46′ ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሯል፡፡

የመጀመርያው አጋማሽ ያለ ግብ ተጠናቋል፡፡

45′ ለማመን የሚከብዱ ኳሶች ሀድያዎች በበረከት ወ/ዮሐንስ እና እንዳለ ደባልቄ አማካኝነት አመከኑ ። መጀመርያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ 1 ተጨማሪ ደቂቃ ተሰጥቷል ።
35′ በመጀመርያ ሀያ አምስት ደቂቃ ውስጥ የነበረው ወደ ጎል የመድረስ ፍጥነት እና እንቅስቃሴ ተጋግሎ የቀጠለ ቢሆንም በሁለቱም በኩል ይህ ነው የሚባል ጠንካራ የጎል ሙከራ ማስተናገድ ግን አልቻለም።

25′ ሀድያዎች በተደጋጋሚ ወደ ጎል በመድረስ ተጭነው  እየተጫወቱ  ይገኛሉ ። 13ኛው ደቂቃ ላይ የሀድያው ዕርቅሁን ተስፋዬ ከመዐዘን የተሻገረውን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ የወጣው የጨዋታው  የመጀመርያ  ሙከራ ነው፡፡
10′ ሀለባ ከነማ የሀድያ ሆሳህናው ሄኖክ አርፊጮ የቀይ ካርድ ቅጣቱን ሳይጨርስ ነው የተሰለፈው በማለት ክስ  ሀላባዎች አሲዘው የጀመረው ጨዋታው አሁን 10 ኛው ደቂቃ የደረሰ ሲሆን በሁለቱም በኩል ብርቱ ፉክክር እየተመለከትን እንገኛለን:: 

ተጀመረ!

ጨዋታው ተጀምሯል፡፡ አስገራሚ የደጋፊዎች ድባብ በስታድየሙ እየታየ ይገኛል፡፡


08:45 ሶስቱም ስታድየሞች ማለትም የመቀለው ትግራይ ስታድየም ፣ የጅማ ስታድየም እንዲሁም የሆሳዕናው አቢዮ አርሳሞ ስታድየም በሀመልካች ተሞልተዋል፡፡ ከ15 ደቂቃ በኋላ ጨዋታዎቹ ይጀመራሉ፡፡


ጤና ይስጥልን ክበራት እና ክቡራን!


በዛሬው እለት የሚካሌዱ የከፍተኛ ሊግ ሶስት ወሳኝ ፍልሚያዎች ወደ ፕሪምየር ሊጉ የሚያድጉ ሁለት ቡድኖችን ይለያል፡፡ ሶከር ኢትዮጵያም በሶስቱ ጨዋታዎች ላይ ተገኝታ ማረጃዎችን ወደ እናንተ ለማድረስ ዝግጅቷን አጠናቃለች፡፡

ዳዊት ጸኃዬ ከ መቀለ
ዳንኤል መስፍን ከ ሆሳዕና
ሚካኤል ለገሰ ከ ጅማ በቀጥታ የየጨዋታዎቹን መረጃዎች ያደርሷችኋል፡፡

መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *