ቻን 2018 | ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ወደ ጅቡቲ የሚጓዙ ተጫዋቾች ታውቀዋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ2018 ቻን ቅድመ ማጣርያ ከጅቡቲ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ተጫዋቾቻቸውን በመያዝ ላለፉት 2 ሳምንታት በድሬዳዋ ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ በመጪው ቅዳሜ 09:00 ላይ የመጀመርያውን ጨዋታ የሚያደርግ ሲሆን ሀሙስ ጠዋት ወደ ጅቡቲ የሚያቀና ይሆናል፡፡ በልምምድ ላይ የቆዩት 16 ተጫዋቾችን ጨምሮ ዘግይተው ቡድኑን የተቀላቀሉት አሜ መሀመድ ፣ ብሩክ ቃልቦሬ እና ተስፋዬ በቀለ አብረው ከቡድኑ ጋር የሚጓዙ ሲሆን የመከላከያው አጥቂ ምንይሉ ወንድሙ በልምምድ ላይ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት አብሮ የመጓዙ ጉዳይ አጠራጣሪ ሆኗል፡፡

ለዝግጅቱ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተመርጠው የነበሩት አስቻለው ታመነ ፣ ሳላዲን በርጊቾ ፣ ሳላዲን ሰኢድ ፣ ምንተስኖት አዳነ ፣ ናትናኤል ዘለቀ እና በኃይሉ አሰፋ ከቡድናቸው ጋር ለቻምፒየንስ ሊግ ወደ ቱኒዝ በማቅናታቸውና ወደ አዲስ አበባ የሚመለሱትም ነገ በመሆኑ ወደ ጅቡቲ እንደማያቀኑ ተረጋግጧል፡፡

ወደ ጅቡቲ የሚጓዙ ተጫዋቾች ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች

ጀማል ጣሰው (ጅማ አባ ቡና) ፣ ሳምሶን አሰፋ (ድሬዳዋ ከተማ) ፣ ለአለም ብርሃኑ (ሲዳማ ቡና)

ተከላካዮች

አብዱልከሪም መሃመድ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ አንተነህ ተስፋዬ (ሲዳማ ቡና) ፣ ሙጂብ ቃሲም (አዳማ ከተማ) ፣ ተስፋዬ በቀለ (አዳማ ከተማ) ደስታ ዮሀንስ (ሀዋሳ ከተማ) ፣ አምሳሉ ጥላሁን (ፋሲል ከተማ)

አማካዮች

ሽመክት ጉግሳ (ደደቢት) ፣ ሙሉአለም መስፍን (ሲዳማ ቡና) ፣ ጋዲሳ መብራቴ (ሃዋሳ ከተማ) ፣ ታፈሰ ሰለሞን (ሀዋሳ ከተማ) ፣ ብሩክ ቃልቦሬ (አዳማ ከተማ)

አጥቂዎች

ጌታነህ ከበደ (ደደቢት) ፣ አዲስ ግደይ (ሲዳማ ቡና) ፣ አብዱልራህማን ሙባረክ (ፋሲል ከተማ) ፣ አሜ መሀመድ (ጅማ አባ ቡና)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *