​ደደቢት ሁለት ተጫዋቾችን አስፈረመ

አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታን የክለቡ ዋና አሰልጣኝ አድረጎ የቀጠረው ደደቢት የ2 ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል፡፡

ከ2002-2007 በደደቢት ያሳለፈው ታደለ መንገሻ ወደ ክለቡ የሚመልሰውን ዝውውር አድርጓል፡፡ ታደለ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዘመናትን በአርባምንጭ ከተማ ያሳለፈ ሲሆን ደደቢት በውድድር አመቱ ሲቸገር የነበረበትን የጎል እድል የሚፈጥር አማካይ እጥረት ይቀርፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፋሲካ አስፋው ሌላው ለክለቡ ፊርማውን ያኖረ ተጫዋች ነው፡፡ በአዳማ ከተማ ከተማ ሁለት የውድድር አመታት ያሳለፈው አንጋፋው አማካይ እንደ ታደለ ሁሉ የክለቡን የአማካይ ክፍል ችግር ለመቅረፍ የሚያግዝ ዝውውር አድርጓል፡፡

ደደቢት ከሁለቱ ተጫዋቾች በተጨማሪ የመስመር ተከላካዮቹ ስዩም ተስፋዬ እና ብርሀኑ ቦጋለን እንዲሁም የመስመር አጥቂው ሽመክት ጉግሳን ውል ሲያድስ በውሰት ለ6 ወራት በፋሲል ያሳለፈው አቤል ያለውን ለመመለስ እንዳሰበ ታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *