​ጀማል ጣሰው ለድሬዳዋ ከተማ ፈረመ

ጀማል ጣሰው ወደ ድሬዳዋ ከተማ የሚያደርገውን ዝውውር በዛሬው እለት አጠናቋል፡፡

የውድድር ዘመኑን በጅማ አባ ቡና ያሳለፈው ጀማል ጣሰው የአንድ አመት ኮንትራቱ መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ድሬዳዋ ከተማ አምርቷል፡፡ የቀድሞው የኤሌክትሪክ ፣ ሀዋሳ ከተማ ፣ ደደቢት ፣ ኢት ቡና እና መከላከያ ግብ ጠባቂ በምስራቁ ክለብ ለቋሚ ተሰላፊነት ከቡድኑ አምበል ሳምሶን አሰፋ ጋር ከባድ ፉክክር ይጠብቀዋል፡፡

የሳምሶን አሰፋ ተጠባባቂ የነበሩትን ግብ ጠባቂዎች ያሰናበተው ድሬዳዋ በሊጉ ምርጥ ከሚባሉ ግብ ጠባቂዎች መካከል ሁለቱን መያዝ ችሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *