​ወላይታ ድቻ እርቅይሁን ተስፋዬን አስፈርሟል

ወላይታ ድቻ የመሀል ተከላካይ ስፍራ ተጫዋች እርቅይሁን ተስፋዬን አስፈርሟል፡፡  

በ2007 ሙገር ሲሚንቶን ለቆ ሀዲያ ሆሳዕናን የተቀላቀለው ግዙፉ ተከላካይ ዘንድሮ ሀዲያ ወደ ፕሪምየር ሊግ ለመመለስ ከጫፍ ደርሶ ባይሳካለትም በግሉ ጥሩ አመት ማሳለፍ ችሏል፡፡

እርቅይሁን በወላይታ ድቻ ሁለት አመታት ለመቆየት ፊርማውን ያኖረ ሲሆን ቶማስ ስምረቱን ያጣው ወላይታ ድቻም ለተከላካይ መስመሩ ጥንካሬን የሚፈጥር ዝውውር ማድረግ ችሏል፡፡

ወላይታ ድቻ በዝውውር መስኮቱ ከሌላው ጊዜ በተለየ ሁኔታ ተጫዋቾችን በማሰፈረም ላይ የሚገኝ ሲሆን የእርቅይሉን ፊርማ 7ኛው ሆኗል፡፡ በአጥቂ ስፍራ ላይም ሌሎች የሀገር ውስጥ እና ከውጭ ተጨማሪ ተጫዋቾች ለማስፈረም እንቅስቃሴን እያደረገ ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *