​ኃይሌ እሸቱ ለኢትዮ ኤሌክትሪክ ፈረመ

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በዛሬው እለት አጥቂው ኃይሌ እሸቱን በ2 አመታት ኮንትራት አስፈርሟል፡፡

ኃይሌ እሸቱ ያለፉትን ሁለት የውድድር አመታት በአዲስ አበባ ከተማ ያሳለፈ ሲሆን ቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ አስተዋፅኦ ካበረከቱ ተጫዋቾች አንዱ ነበር፡፡ አአ ከተማ ባደገበት አመት ወደ ከፍተኛ ሊጉ ቢመለስም ኃይሌ በግሉ መልካም የውድድር አመት ማሳለፍ የቻለ ሲሆን ቡድኑ ባስመዘገባቸው ነጥቦች ላይም ግቦቹ ወሳኞች ነበሩ፡፡

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በአጥቂ ክፍሉ ላይ ጠባብ የተጫዋቾች አማራጭ የነበረው ኤሌክትሪክ በኃይሌ መፈረም ምክንያት ይጠናከራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ኤሌክትሪክ በዝውውር መስኮቱ ከአጥቂው ኃይሌ በተጨማሪ ግብ ጠባቂውዮሀንስ በዛብህ ፣ ተከላካዮቹ ግርማ በቀለ እና ሞገስ ታደሰ እንዲሁም አማካዮቹ ኄኖክ ካሳሁን እና ጥላሁን ወልዴን ማስፈረም ችሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *