​የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ቅዳሜ ይጀመራል

ወደ አንደኛ ሊግ የሚያልፉ ክለቦችን ለመለየት የሚደረገው የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና በወልድያ ከተማ አስተናጋጅነት ከሐምሌ 22-ነሐሴ 7 ይካሄዳል፡፡

የውድድሩ የእጣ ማውጣት ስነ ስርአት በነገው እለት የሚካሄድ ሲሆን ከ9 ክልሎች እና 2 የከተማ መስተዳድር ውድድሮች የተውጣጡ 34 ክለቦችም በውድድሩ ላይ የሚካፈሉ ይሆናል፡፡ ሆኖም እስካሁን ውድድሩ ላይ እንደሚካፈሉ ማረጋገጫ የሰጡ 19 ክለቦች መሆናቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ገልጿል፡፡

በወልድያ በሚካሄደው በዚህ ውድድር ላይ ወደ ሩብ ፍጻሜው የሚቀላቀሉ 8 ቡድኖች ወደ ኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ማለፋቸውን ያረጋግጣሉ፡፡

አምና ውድድሩ በአርባምንጭ የተካሄደ ሲሆን ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ (ፎቶ) በአሸናፊነት ማጠናቀቁ የሚታወስ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *