​መቐለ ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሟል

ከፍተኛ ሊጉን በ3ኝነት አጠናቆ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ያደገው መቐለ ከተማ የ2 ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል፡፡

ከፕሪምየር ሊጉ የወረደው ኢትዮጵያ ንግደ ባንክ ጋር የነበራቸው ውል የተጠናቀቀው የመስመር ተከላካዮቹ ዳንኤል አድሐኖም እና አንተነህ ገብረክርስቶስ ክለቡን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

የግራ መስመር ተከላካዩ አንተነህ ገብረክርስቶስ በ2007 ክረምት አዳማ ከተማን ለቆ ንግድ ባንክን ከተቀላቀለ በኋላ ዘንድሮ በጭንቅላቱ ላይ በደረሰበት ጉዳት ለጥቂት ጊዜያት ከሜዳ እስኪርቅ ድረስ መደበኛ ተሰላፊ የነበረ ሲሆን የቀኝ መስመር ተከላካዩ ዳንኤል አድሐኖም ደግሞ በንግድ ባንክ ቆይታው አልፎ አልፎ በመጀመርያ አሰላለፍ አመዛኙን ጊዜ ደግሞ በተጠባባቂነት ያሳለፈ ተጫዋች ነው፡፡

ሁለቱም ተጫዋቾች ለመቐለ ከተማ የአንድ አመት ውል የተፈራረሙ ሲሆን በዝውውር መስኮቱም ተቀዛቅዞ ለቆየው መቐለ ከተማ ያስፈረማቸው የመጀመርያዎቹ ተጫዋቾች ሆነዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *