​ሀዲያ ሆሳዕና እዮብ ማለን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል

ወደ ፕሪምየር ሊጉ ለማደግ ከጫፍ ደርሶ በመቐለ ከተማ ተሸንፎ ሳይገባ የቀረው ሀዲያ ሆሳዕና አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው ወደ ባህርዳር ከተማ ማምራታቸውን ተከትሎ አብረዋቸው ያመራሉ ተብለው ሲጠበቁ የነበሩት ረዳታቸው እዮብ ማለ የሀዲያ ሆሳዕና ዋና አሰልጣኝ ሆነው እንዲቀጥሉ ክለቡ ባደረገው የቦርድ ስብሰባ ወስኗል፡፡

በአርባምንጭ ጨጨ ፣ ኮምቦልቻ ጨጨ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ስኬታማ የተጫዋችነት ዘመን ያሳለፉት አሰልጣኝ እዮብ ወደ አሰልጣኝት ሙያ ከመጡ በኋላ በወልቂጤ ከተማ እና ደሴ ከተማ ዋና አሰልጣኝ እንዲሁም በአርባምንጭ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ ሆነው የሰሩ ሲሆን በሀዲያ ሆሳዕና ከተጠናቀቀው አመት መጀመርያ አንስቶ በጳውሎስ ጌታቸው ምክትልነት ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡

እዮብ በሀዲያ ሆሳዕና በ3 የውድድር አመታት የተሾሙ 4ኛ አሰልጣኝ ሆነዋል፡፡ አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ ክለቡን ለፕሪምየር ሊግ ካበቁ ከ6 ወራት በኋላ ሲሰናበቱ ጥላሁን መንገሻ እና ጳውሎስ ጌታቸው በ18 ወራት ወስጥ ክለቡን የመሩ ሌሎች አሰልጣኞች ናቸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *