ኢትዮጵያ የሴካፋ ሲኒየር ቻሌንጅ ዋንጫን በህዳር ወር እኝደምታዘጋጅ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን ፕሬዝደንት ጁነዲ ባሻ በግል የትዊተር ገፃቸው አስተውቀዋል፡፡ የሴካፋ ዋንጫን በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች ለማዘጋጀት መታሰቡን ጁነዲ ጨምረው አስታውቀዋል፡፡ ኢትዮጵያ የሴካፋ ዋንጫን ስታዘጋጅ ይህ ለአራተኛ ግዜ ነው፡፡ ከዚህ በፊት በታህሳስ 1980፣ በህዳር 1997 እና 1999 ውድድሩን አዘጋጅታለች፡፡ የቻን 2020ን ለማዘጋጀት የእግርኳስ ፌድሬሽኑ ከጫፍ መድረሱን ጁነዲ ጨምረው ገልፀዋል፡፡