ወልዋሎ እንየው ካሳሁንን በይፋ አስፈርሟል

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የቀኝ መስመር ተከላካዩ እንየው ካሳሁንን ፊርማ አጠናቋል፡፡

እንየው ከወልዋሎ ጋር የተስማማው ከቀናት በፊት ቢሆንም በአዲስ አበባ ከተማ ቀሪ የአንድ አመት ኮንትራት የነበረው መሆኑ ፊርማውን አዘግይቶት ቆይቷል፡፡ በመጨረሻም እንየው ክለቡ የጠየቀውን የውል ማፍረሻ ገንዘብ በመክፈል መልቀቂያውን በመቀበሉ በይፋ ለወልዋሎ ፊርማውን ማኖር ችሏል፡፡

ፌዴራል ፖሊስን ለቆ አዲስ አበባን ከተቀላቀለ ወዲህ በክለቡ 3 የውድድር ዘመናትን ያሳለፈ ሲሆን በኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ቡድን ውስጥም መካተት ችሎ ነበር፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *