ታዲዮስ ወልዴ ለአርባምንጭ ከተማ ፈርሟል  

አርባምንጭ ከተማ በክረምቱ ዝውውር መስኮት ሁለተኛ ዝውውሩን በማከናወን የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ታዲዮስ ወልዴን አስፈርሟል፡፡

ታዲዮስ ወልዴ በ2004 ድሬዳዋ ከተማን ለቆ ያለፉትን 6 የውድድር ዘመናት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያሳለፈ ሲሆን የመጨረሻዎቹን ሁለት የውድድር ዘመናትም በአምበልነት ሲያገለግል ቆይቶ ክለቡን በመልቀቅ ወደ አርባምንጭ አምርቷል፡፡ በክለቡም ከቀድሞ አሰልጣኙ ጸጋዬ ኪዳነማርያም ጋር የሚገናኝ ይሆናል፡፡

አርባምንጭ ከታዲዮስ በተጨማሪ ግብ ጠባቂው ሲሳይ ባንጫን ባለፈው ሳምንት ማስፈረሙ ይታወሳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *