ኢትዮጵያ ቡና 3 ተጫዋቾችን የግሉ አድርጓል

ኢትዮጵያ ቡና በዛሬው እለት የሶስት ተጫዋቾችን ፊርማ አጠናቋል፡፡ አስራት ቱንጆ ፣ ሮቤል አስራት እና አብዱሰላም አማን ለክለቡ ፊርማቸውን ያኖሩ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

አስራት በውድድር አመቱ ጅማ ከተማ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን ከአማካይ ስፍራ እየተነሳም ወሳኝ ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል፡፡ ሌላው በጅማ ከተማ ድንቅ አመት ማሳለፍ የቻለው ሮቤል አስራት የግራ መስመር ተከላካይ ሲሆን በቦታው ወደፊት ትልቅ ተስፋ ከሚጣልባቸው ተጫዋቾች አንዱ ነው፡፡

አብዱሰላም አማን እንደ ሁለቱ ተጫዋቾች ሁሉ በከፍተኛ ሊጉ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲያልፍ ከፍተኛ ሚና መጫወት የቻለ የመስመር አማካይ ስፍራ ተጫዋች ነው፡፡

ክለቡ በክረምቱ በተለይም ከከፍተኛ እና አንደኛ ሊጉ በርካታ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ከስምምነት ቢደርስም በይፋ ማስፈረም የቻለው ከላይ የተጠቀሱትን ጨምሮ 7 ተጫዋቾችን ነው፡፡


ፎቶ ፡ ከላይ ሮቤል አስራት ፣ መካከል ላይ አብዱሰላም አማን እና ከታች አስራት ቱንጆ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *