የሴቶች ዝውውር ፡ መከላከያ ሁለት ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የወሳኝ ተጫዋቾቹን ውል አድሷል  

የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ የሆነው መከላከያ ሁለት ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የሁለት ወሳኝ ተጫዋቾችን ውል ማደስ ችሏል፡፡

የአጥቂ መስመር ተሰላፊዋ መዲና አወል ለመከላከያ የፈረመች ተጫዋች ናት፡፡ ባለፉት የውድድር ዘመናት በቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ድንቅ አቀሟን ስታሳይ የቆየችው መዲና አወል ከበርካታ ክለቦች ጋር ስሟ ሲያያዝ ቆይቶ በመጨረሻም ማረፊያዋን መከላከያ አድርጋለች፡፡

ሌላዋ ክለቡን የተቀላቀለችው ተጫዋች የተከላካይ መስመር ተሰላፊ የሆነችው ፋሲካ በቀለ ናት፡፡ ፋሲካ በቀድሞው ዳሽን ቢራ እና ክለቡ ከፈረሰ በኋላ ቡድኑን በተረከበው ጥረት ኮርፖሬት ጥሩ የውድድር ጊዜያት ካሳለፈች በኋላ ኮንትራቷን አጠናቃ ወደ ጦሩ አምርታለች፡፡

መከላከያ ካስፈረማቸው ተጫዋቾች በተጨማሪ የቡድኑ ቁልፍ ተሰላፊዎች የሆኑት የመስመር አማካይዋ የምስራች ላቀው እና የመሀል አማካይዋ እመቤት አዲሱን ውል ማደሱን ክለቡ አስታውቋል፡፡

እመቤት አዲሱ
የምስራች ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *