አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈርሟል

ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ራሱን ለማጠናከር ዘግይቶም ቢሆን ወደ ዝውውር ገበያው የገባው አርባምንጭ ከተማ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጪ ተጫዋች በማስፈረም ጋናዊው የፊት መስመር ተጫዋች ሰይዱ ባንሴን በአንድ አመት ውል ወደ ክለቡ አምጥቷል፡፡

አጥቂው ከ2010 ጀምሮ በሀገሩ ክለብ ኡቡሰዋ ዱዋርፍስ ለሁለት አመት ከተጫወተ በኃላ ወደ ጋናው ኃያል ክለብ አሻንቲ ኮ ቶኮ የተዛወረ ሲሆን ለግብፁ ሰምሀ ክለብም መጫወት ችሏል፡፡ ለሀገሩ ጋና ከ23 አመት በታች (ኦሎምፒክ ቡድን) ሲጫወት በ2014 የጋና ብሔራዊ ቡድንን በቻን መወከልም ችሏል፡፡

አርባምንጭ ከተማ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከሰይዱ በተጨማሪ ሲሳይ ባንጫ ፣ ዮናታን ከበደ እና ታዲዮስ ወልዴን ያስፈረመ ሲሆን ተጨማሪ አንድ ተጫዋች ከጋና ለማምጣትም ጥረት ላይ ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *