ፍፁም ገብረማርያም ወደ ወልድያ አምርቷል

በዘንድሮው የዝውውር ሂደት ወስጥ በሰፊው ከተሳተፉ ክለቦች መሀከል አንዱ የሆነው ወልድያ ላለፈው አንድ አመት ከግማሽ ያህል በኢትዮ ኤሌክትሪክ ያሳለፈው ፍፁም ገብረማርያምን ማስፈረም ችሏል።

በሳለፍነው የውድድር አመት ከፍተኛ ግብ የማስቆጠር ችግር የተስተዋለበት ወልድያ በሊጉ ለመቆየት ከማጥቃቱ ይልቅ የመከላከል ጥንካሬው ላይ የተመረኮዘ ይመስል ነበር። አዲሱን የውድድር አመት ከአሰልጣኝ ዘማርያም ጋር የሚጀመረው ክለቡ ይህንን ችግሩን ለማስተካከል ከ ኤደም ሆሮውሶቪ በመቀጠል የቀድሞውን የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የሙገር አጥቂ በእጁ ማስገባቱም ደካማ ጎኑን ለማሻሻል እንደሚጠቅመው ይጠበቃል።

ፍፁም ገብረማርያም በዘንድሮው የውድድር አመት 11 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን በቀድሞ ክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስም ለሶስት የውውድር አመታት መልካም ቆይታ ነበረው። ተጨዋቹ በሚቀጥለው አመት በሰማያዊ እና ነጭ ለባሾቹ ቤት የምናየው 12ኛ አዲስ ፈራሚ ሆኗል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *