የኢትዮጵያ ተጋጣሚ ኬንያ ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን የአቋም መለኪያ ጨዋታ ያደርጋል

ፈረንሳይ በፈረንጆቹ 2018 ለምታስተናግደው የፊፋ የሴቶች ከ20 ዓመት በታች አለም ዋንጫ ለማለፍ የሚደረጉ የአፍሪካ ዞን የማጣሪያ ጨዋታዎች በመስረም ወር ይቀጥላሉ፡፡ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቅጥር እና ለዝግጅት ተጫዋቾች የተመረጡት በያዝነው ሳምንት ሲሆን መስረም 7 ኢትዮጵያን ድሬዳዋ ላይ በማጣሪያው የምትገጥመው ኬንያ ግን በጠንካራ ዝግጅትላይ ከመገኘቷ ባሻገር የአቋም መለኪያ ጨዋታ ለማድረግ ተዘጋጅታለች፡፡

ኬንያ በቅድመ ማጣሪያ ዙሩ ቦትስዋናን ከሜዳዋ ውጪ 7-1 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር በቀላሉ ማለፍ ስትችል የመልስ ጨዋታው የቦትስዋና ብሄራዊ ቡድን በፋይናንስ እጥረት ራሱን ከውድድር በማግለሉ ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡

ኬንያ ነሃሴ 23 እና 25 ላይ ከዮርዳኖስ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሄራዊ ቡድን ጋር ሁለት የአቋም መለኪያ ጨዋታ ለማድረግ ቀነ ቀጠሮ መያዙን የኬንያ እግርኳስ ፌድሬሽን አስታውቋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ማቻኮስ ላይ ቡድኑ 33 ተጫዋቾችን በመያዝ ዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

የኬንያ እግርኳስ ፌድሬሽን አፍሪካ ዞን የማጣሪያ ጨዋታዎች ይፋ ከመሆናቸው አስቀድሞ ከኢትዮጵያ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ያደረገው ጥረት በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን ተቀባይነት አለማግኘቱን ተከትሎ ሳይካሄድ ቢቀርም የነገሮች መገጣጠምን ተከትሎ ሁለቱ ሃገራት በማጣሪያው አንደኛ ዙር ተፋጠዋል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ዩራጓይ ለምታስተናግደው የፊፋ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ዓለም ዋንጫም ኢትዮጵያ እና ኬንያ ዳግም ይገናኛሉ፡፡

ኬንያ በመስረም 2016 ዩጋንዳ ላይ የተዘጋጀው የሴካፋ ሴቶች ቻምፒዮና ላይ እስከፍፃሜ ስትደርስ በዛው አመት በአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ላይ ተሳትፎ አድርጋለች፡፡ በምስራቅ አፍሪካም በአሁኑ ሰዓት በሴቶች እግርኳስ ከፍተኛ መሻሻልን ካሳዩ ሃገራት መካከል በቀዳሚነት ትጠቀሳለች፡፡

የኬንያ ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ስብስብ

ግብ ጠባቂዎች
ሊሊያን አዉር፣ ጁዲ ኦሲምቦ (ናያካች ገርልስ)፣ ዲና ቴምቤሲ (ዊይታ ገርልስ)፣ አይቪ ማኮካ (ኢቢንዞ ገርልስ)

ተከላካዮች
ዊንኬት ካሪ (ቲካ ኩዊንስ)፣ ሊ ቼሮቲች፣ ሮቢ ሻሪ፣ ማውሪን ካካሳ (ዊይታ ገርልስ)፣ ቬሮኒካ አዊኖ (ደማስከስ ፕሪ)፣ አሊስ ሚዲሪ (ኢቢንዞ ገርልስ)፣ ሉሲ አኮት (ሴንት ፖልስ ኤቦዎ)፣ ቪቪየን ማኮካ (ኢቢንዞ ገርልስ)፣ ዚፖራ አዲአምቦ (ታርታር ገርልስ)፣ ፎስካ ናሺቫንዳ (ንጊንዳ ገርልስ)፣ ሚሊሰንት አጄማ (ቤሾፕ ኦኪሉ)

አማካዮች
ኮራዞን አኩዊኖ (ሳከር ክዊንስ)፣ ሼርሊ አንጋቺ (ኦሎምፒክ ሃይ)፣ ሲንቲያ ሺልዋትሶ (ኢቢንዞ ገርልስ)፣ ሲንቲያ አኪኒ (ንጊንዳ ገርልስ)፣ ሲንቲያ አልዋላ (ማይና ዋንጂጊ)፣ ቴሬሳ ጋኪ (ክዋሌ ገርልስ)፣ ዶራ አቼንግ (ኦሎምፒክ ሃይ)፣ ቲና ተርነር ዋሪሙ (ሴንት ፖልስ ኤቦዎ)፣ ጆአን አኮት (ሴፕ ኪሲሙ)

አጥቂዎች
መርሲ አይሮ (ናያካች ገርልስ)፣ ሊሊያን ምቦጋ (ኢቢንዞ ገርልስ)፣ ሬቾል ሙኤማ (ቲካ ክዊንስ)፣ ማርታ አሙንዮሌቴ (ዊይታ ገርልስ)፣ ዳያና ዋሴራ (ማታር ዩናይትድ)፣ ክሪስቲን ኪታሩ (ንጊንዳ ገርልስ)፣ ስቴላ አንያንጎ (ሳከር ክዊንስ)፣ ፌዝ አቲኖ (ኦሎምፒክ ሃይ)፣ ጌንትሪክ ሺካንግዋ (ዊይታ ገርልስ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *