በረከት ይስሀቅ ለኢትዮጵያ ቡና ፈረመ

ኢትዮጵያ ቡና እያካሄደ በሚገኘው የቅድመ ውድድር ዝግጅት ላይ የሙከራ እድል የሰጠው በረከት ይስሀቅን አስፈርሟል፡፡

አሰልጣኝ ድራጋን ፖፓዲች ቡድናቸውን በሀዋሳ ለቀጣዩ የውድድር አመት እያዘጋጁ የሚገኙ ሲሆን በረከት ይስሀቅም በአሰልጣኙ የሙከራ ጊዜ ተሰጥቶት ያለፉትን ቀናት ከቡድኑ ጋር ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በቆይታውም አሰልጣኝ ፖፓዲችን ማሳመን በመቻሉ በአንድ አመት ኮንትራት ክለቡን መቀላቀል ችሏል፡፡

የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ፣ ኤሌክትሪክ እና ደደቢት አጥቂ የውድድር ዘመኑን በአንድ አመት ውል በድሬዳዋ ከተማ ያሳለፈ ሲሆን ካለፉት የውድድር ዘመናት በአንጻራዊነት መሻሻል ማሳየት የቻለበትን ጊዜ አሳልፏል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ከበረከት ይስሀቅ በተጨማሪ ለቀድሞው የመከላከያ እና ኤሌክትሪክ አጥቂ ማናዬ ፋንቱ የሙከራ እድል የሰጠ ሲሆን እንደ በረከት ሁሉ አሰልጣኙን ማሳመን ከቻለ ውል እንደሚቀርብለት ታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *