ሰበታ ከተማ ዘጠኝ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

ከ2001-2003 በፕሪምየር ሊግ የቆየው ሰበታ ከተማ ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ለመመለስ በከፍተኛ ሊጉ በ2010 ለሚኖረው ተሳትፎ በዝውውሩ ጠንካራ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል ።

አሰልጣኝ ስዩም ከበደን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ የሾመው ሰበታ ከተማ እስካሁን ባለው የዝውውር ሂደት ውስጥ ዘጠኝ ተጫዎችን አስፈርሟል፡፡ ከዛህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ በአሰልጣኙ ስር የሰሩ ተጫዋቾችም ክለቡን ተቀላቅለዋል፡፡

የፈረሙት ተጫዋቾት ዝርዝር እና ቀድሞ የነበሩበት ክለብ የሚከተሉት ናቸው፡-

ኄኖክ ካሳሁን (የግራ መስመር ተከላካይ – ባህርዳር ከተማ) ፣ ዘሪሁን ብርሃኑ (የተከላካይ አማካይ – አአ ከተማ) ፣ ዜናው ፈረደ (የተከላካይ አማካይ – መቐለ ከተማ) ፣ ሐብታሙ ረጋሳ (የአጥቂ አማካይ ፣ መድን) ፣ አዲስአለም ተስፋዬ የአጥቂ አማካይ – ኢት/ውሃ ስራ) ፣ ኤፍሬም ቀሬ (አጥቂ – አአ ከተማ) ፣ ኄኖክ መሀሪ (አጥቂ – ጅማ ከተማ) ፣ ጌዲዮን ታደሰ (አጥቂ ፣ መቐለ ከተማ) ፣ አብይ ቡልቲ (አጥቂ – መድን)

ክለቡ ካስፈረማቸው ተጫዋቾች ባሻገር ተጨማሪ ተጨዋቾችን እንደሚያስፈርሙ ለማወቅ የቻልን ሲሆን በቡድኑ ውስጥ አምና በነበረው የከፍተኛ ሊግ ውድድር ላይ ኮንትራታቸው ያላለቁ ተጨዋቾች ከክለቡ ጋር ይቆያሉ ተብሏል ።

አሰልጣኝ ስዮም ከበደ አአ ከተማን ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪምየር ሊግ ያስገቡበትን እና የረጅም ጊዜ የማሰልጠን ልምዳቸውን ተጠቅመው ሰበታ ከተማን ወደ ፕሪምየር ሊግ ሊያስገቡት ይችላሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ አሰልጣኙም በ2010 ጥቅምት 11 ይጀመራል ለተባለው የከፍተኛ ሊግ የውድድር ዘመን ዝግጅታቸውን የሚጀምሩበት እቅድ ያወጡ ሲሆን ከመስከርም ሁለት አንስቶ ዝግጅታቸውን በይፋ እንደሚጀምሩ ታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *