መከላከያ ምንያምር ጸጋዬን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ

መከላከያ ስፖርት ክለብ ተስፋ ቡድንን ከ2005-2006 ያሰለጠኑትና ከ2007 – 2009 ድረስ በዋናው ቡድን በምክትል አሰልጣኝነት ያሳለፉት አሰልጣኝ ምንያምር ጸጋዬ የክለቡ ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሹመዋል፡፡

በ2009 መከላከያን በዋና አሰልጣኝነት ሲያገለግሉ የነበሩት አሰልጣኝ በለጠ ገ/ኪዳን የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን ም/አሰልጣኝ ሆነው በመመረጣቸውን ተከትሎ መከላከያን በጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት ሲያገለግሉ የነበሩት ምንያምር ቡድኑን ለቀጣይ የውድድር ዘመን ዋና አሰልጣኝ ሆነው እንዲመሩ መሾማቸውን ክለቡ በይፋዊ ደደብዳቤ አረጋግጧል። የአሰልጣኝ ምንያምር ረዳት በመሆን ደግሞ ከ20 አመት በታች ቡድኑ አሰልጣኝ መንግስቱ ዋጫ ሆነው ተመርጠዋል፡፡

መከላከያ በ2009 አመት በ37 ነጥብ ስምንተኛ ሆኖ የጨረሰ ሲሆን ለቀጣይ አመት የውድድር ዘመን ዝግጅቱን በቢሸፍቱ ከተማ አየር ኃይል ሜዳ በአሰልጣኝ ምንያምር እየተመራ እየተዘጋጀ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *