የደቡብ ክልል ካስትል ዋንጫ መስከረም 13 እንዲጀመር ተወስኗል

የደቡብ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በየአመቱ የሚያዘጋጀው የደቡብ ክልል ካስትል ዋንጫ ከመስከረም 6-14 ይደረጋል ተብሎ መርሃ ግብር የወጣለት ቢሆንም ክለቦች በበአል ምክንያት ቡድናቸውን መበተናቸውን ተከትሎ ለፌደሬሽኑ ባቀረቡት ጥያቄ መራዘሙ ይታወሳል፡፡ አሁን ደግሞ የእግርኳስ ፌዴሬሽኑ ዛሬ ለሶከር ኢትዮጵያ እንዳስታወቀው ከሆነ ውድድሩ ከመስከረም 13-21 እንዲከናወን ቀን ተቆርጦለታል፡፡

በተጋባዥነት እስከ አሁን ኢትዮጵያ ቡና እና ፋሲል ከተማ እንደሚካፈሉ አስቀድሞ የታወቀ ሲሆን አሁን ደግሞ ድሬዳዋ ከተማ ሌላኛው ተሳታፊ መሆኑ መረጋገጡን የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ደመላሽ ይትባረክ ለሶከር ኢትዮጵየያ ገልጸዋል፡፡ የወልዲያ እና የጅማ አባ ጅፋር ተሳታፊነትም በሁለህ ቀናት ውስጥ ቁርጡ ይለያል ብለዋል፡፡

ለ6ኛ ጊዜ የሚደረገውና ካስትል ቢራ የስያሜ መብቱን የገዛው ይህ ውድድር ከመክፈቻው አንድ ቀን ቀደም ብሎ የእጣ ማውጣት ስነስርአቱ እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *