የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በአአ እግርኳስ ፌዴሬሽን ውዝግብ ዙርያ ውሳኔ አሳለፈ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እግር ኳስ ፌደሬሽን የ2009 ጠቅላላ ጉባኤውን ነሃሴ 20 በኢትዮጵያ ሆቴል ማከናወኑ ይታወቃል፡፡ ሆኖም የተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ህጋዊ አደለም በሚል ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ጠቅላላ ጉባኤው በድጋሚ እንዲደረግ እና በእለቱ በተወሰኑት ውሳኔዎች ላይ ፌደሬሽኑ እውቅና እንዳይሰጥ በመጠየቁ ፌደሬሽኑ ጉዳዩን ሲመለከት ቆይቷል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዛሬ እንዳስታወቀው በሁለቱም ወገኖች በኩል የቀረቡትን መረጃዎች ከተመለከተ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤው ህጋዊ እንደሆና እንውቅናም እንደሚሰጠው ገልጻል፡፡ ነሃሴ 20 በተደረገው ጠቅላላ ጉባኤ የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን የስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ ሰላሙ በቀለ ፣ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ገ/ማርያም እና ምክትል ፕሬዝዳንቱ አቶ ኃይሉ ሞላን ከስራቸው ማንሳቱ የሚታወስ ሲሆን የፌደሬሽኑ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ አማረ ማሞ በግል ጉዳይ ምክንያት በራሳቸው ፍቃድ ከመንበራቸው መነሳታቸው ይታወቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *