ለገጣፎ ለገዳዲ በለቀቁበት ተጫዋቾች ምትክ በማስፈረም ላይ ይገኛል

ባለፈው የውድድር ዓመት ወደ ከፍተኛ ሊጉ ያደገውና ለብዙዎች ፈታኝ ቡድን ሆኖ በመቅረብ በምድብ ሀ 4ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ለገጣፎ ለገዳዲ የአስደናቂ ጉዞው ሰለባ የሆነ ይመስላል፡፡ የአሰልጣኝ ያሬድ ቶሌራ ስብስብ ውስጥ በውድድር አመቱ ምርጥ አቋማቸውን ያሳዩ ተጫዋቾች ወደተለያዩ የከፍተኛ ሊግ ክለቦች ማምራታቸውን ተከትሎ ክለቡ ተተኪ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ ተጠምዷል፡፡

ለገጣፎ ያስፈረማቸው ተጫዋቾች እና የቀድሞ ክለቦቻቸው እነዚህን ይመስላሉ፡-

እሽቱ ከበደ (ወሎ ኮምቦልቻ / ተከላካይ) ፣ ታመነ ቅባቱ (ሞጆ ከተማ / ተከላካይ) ፣ ዘካያስ ከበደ (*ፎቶ/ ቅዱስ ጊዮርጊስ / አማካይ ) ፣ በሱፍቃድ ነጋሽ (ሰበታ ከተማ / አማካይ) ፣ አዳነ ተካ (ደደቢት / አማካይ) ፣ መክብብ ወልዱ (አክሱም ከተማ / አማካይ) ፣ ደርብ ጀማ (ሰሜንሸዋ ደብረ ብርሃን /አማካይ) ፣ ሐብታሙ ፍቃዱ (ባቱ ከተማ / አማካይ) ፣ ፋሲል አስማማው (ወሎ ኮምቦልቻ /አማካይ) ፣ ሱራፌል አየለ (አክሱም ከተማ / አጥቂ)

ለገጣፎ ለገዳዲ በትላንትናው እለት የቅድመ ውደድድር ዝግጅቱን በባቱ ከተማ በይፋ ጀምሯል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *