​ኢትዮጵያ ኮንስራክሽን ስራዎች ስብስቡን በአዲስ መልክ እያዋቀረ ይገኛል

ባለቤትነቱን ሙሉ ለሙሉ ከኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት በመረከብ ስያሜውንም ወደ ድርጅቱ ስያሜ የለወጠው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ስፖርት ክለብ በቡድን ስብስቡ ላይ የጎላ ለውጥ በማድረግ 18 አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

የውድድር አመቱን በምድብ ሀ ሰንጠረዥ ወገብ ላይ ሆኖ ያጠናቀቀው ክለቡ ከሌሎቹ የከፍተኛ ሊግ ክለቦች በበለጠ በርካታ ተጫዋቾችን ከማስፈረሙ በተጨማሪ በፕሪምየር ሊጉ ሲጫወቱ የነበሩ ተጫዋቾችንም የቡድኑ አባል አድርጓል፡፡

ክለቡ ያስፈረማቸው ተጫዋቾች እና የቀድሞ ክለቦቻቸው የሚከተሉት ናቸው:-

ግብ ጠባቂ

የራስወርቅ ተረፈ (አማራ ውሃ ስራ)

ተከላካዮች

ፍቃዱ ታደሰ (አማራ ውሃ ስራ) ፣ በክሪ መሐመድ (ሽረ እንዳስላሴ) ፣ ይበልጣል ሽባባው (ሰሎዳ አድዋ) ፣ ዳግም ንጉሴ (ወላይታ ድቻ)

አማካዮች

አሳምነው አንጀሎ (ወላይታ ድቻ) ፣ ሚኪያስ ፍቅሬ (ደደቢት) ፣ አቤል ታሪኩ (ሱሉልታ ከተማ) ፣ አቡበከር ፋንታ (አዊ አምፒልታቅ) ፣ በረከት ጥጋቡ (አማራ ፖሊስ) ፣ ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊ (ወልድያ) ፣ አንዋር አብዱጀሊል (አማራ ውሃ ስራ) ፣ ተስፋዬ ታምራት (ኮንሶ ኒውዮርክ)

አጥቂዎች

ሐብቶም ገብሬ (ደሴ ከተማ) ፣ ብሩክ ሀዱሽ (ሽረ እንዳስላሴ) ፣ የኋላሸት ሰለሞን (ዲላ ከተማ) ፣ ሙሴ ተክለወይኒ (ንግድ ባንክ) ፣ አማኑኤል ሐብታሙ (ድሬዳዋ ከተማ)

ክለቡ ከ2009 ስብስቡ መካከል ውላቸው የተጠናቀቁ 9 ተጫዋቾችን ውል ሲያድስ የዘንድሮው የውድድር አመት ቅድመ ዝግጅቱንም በአሰልጣኝ ደግአረገ እየተመራ በዱከም ከተማ ሀሙስ እለት ጀምሯል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *