​ኢትዮጵያውያን አሰልጣኞች የሞሮኮ ስልጠናቸውን አጠናቀው ተመለሱ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ከሞሮኮ እግርኳስ ፌደሬሽን ጋር በመተባበር ለ19 ኢትየጵያዊያን አሰልጣኞች ያዘጋጀው ስልጠና ተጠናቋል። አሰልጣኞቹም ለ2 ሳምንታት ያደረጉትን ስልጠና አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል፡፡

በሞሮኮ ራባት ከተማ በተዘጋጀው ስልጠና በኢትየጵያ የተለያዩ የሊግ እርከኖች የሚገኙ ወንድ እና ሴት አሰልጣኞች ተካፋይ ሲሆኑ በስልጠናውም አዳዲስ የአሰለጣጠን መንገዶችን ቀስመዋል ተብሏል፡፡

ለ15 ቀናት በቆየው ስልጠና የክፍል ውስጥ እና የመስክ ስልጠናዎች እንደተሰጡ ሲገለፅ በተለይ በወጣቶች እግርኳስ ላይ ምን አይነት ስልጠና መሰጠት እንዳለበት በርካታ አዳዲስ ትምህርቶችን እንዳገኙ ሰልጣኞች ተናግረዋል።

ሰልጣኞቹ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ስልጠናቸውን መጨረሳቸውን ተከትሎ ትላንት ምሽት ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸው ሲገለፅ በሞሮኮ በነበራቸው ቆይታ የተለያዩ ጉብኝቶችን ጨምሮ ከሞሮኮ የእግርኳስ አሰልጣኞች ጋር የልምድ ልውውጥ ማድረጋቸው ታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *