​ሽመልስ በቀለ የአመቱ የመጀመርያ ጎሉን አስቆጥሯል

የግብጽ ፕሪምየር ሊግ 3ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ መደረግ ሲጀምሩ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ሽመልስ በቀለ እና ፔትሮጄት የውድድር አመቱን የመጀመርያ ጎል እና ድል አስመዝግበዋል፡፡

ዛሬ አመሻሽ ላይ በፔትሮስፖርት ስታድየም ኤንፒ ፔትሮጄትን አስተናግዶ 2-0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡ በጨዋታው ሽመልሰን በቀለ ሙሉ ክፍለ ጊዜ መሰለፍ የቻለ ሲሆን የእንግዶቹን የመጀመርያ ግብ ወደ እረፍት ሊያመሩ ሽርፍራፊ ሴኮንዶች ሲቀሩ ከዮኤል ላማህ የተሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ ማስቆጠር ችሏል፡፡


ጎሉን ሊንኩን በመጫን ይመልከቱ | LINK


ከዚህ ጨዋታ በመቀጠል ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ኡመድ ኡኩሪ የሚጫወትበት ስሞሀ  አሌክሳንድሪያ ላይ አል ናስርን አስተናግዶ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡ በጨዋታው ኡመድ ለ60 ደቂቃዎች በሜዳ ላይ ቆይቶ በባኑ ዲያዋራ ተቀይሮ ከሜዳ ወጥቷል፡፡ ኡመድ በመጀመርያው ሳምንት ጨዋታ የቀድሞ ክለቡ ኤንፒ ላይ ጎል ማስቆጠሩ የሚታወስ ነው፡፡

የሊጉ 3ኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎች ነገም ሲቀጥሉ በደረጃ ሰንጠረዡ ስሞሀ በ5 ነጥቦች 2ኛ ፣ ፔትሮጄት በ4 ነጥቦች 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *