​የደቡብ ክልል ካስትል ዋንጫ ድልድል ይፋ ሆነ 

የደቡብ ክልል ካስትል ዋንጫ እጣ አወጣጥ ስነ ስርአት በሀዋሳ ሴንትራል ሆቴል ዛሬ 10:00 ላይ ተከናውኗል፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ የሆኑ ክለቦች ሊጉ ከመጀመሩ አስቀድሞ ራሳቸውን ለማዘጋጀት ከሚረዷቸው ውድድሮች  አንዱ የሆነው የደቡብ ካስትል ዋንጫ ነገ ይጀመራል፡፡ ዛሬ በሴንትራል ሆቴል የእጣ አወጣጥ ስነ ስርአት ሲደረግም የክለብ አስልጣኞች ፣ ቡድን መሪዎችና የደቡብ ክልል እግር ኳስ ፌድሬሽን ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ወልደ ሚካኤል መስቀሌን ጨምሮ ጥሪ የተደረጋለቸው እንግዶች በመገኘት ስነ ስርአቱን ታድመዋል፡፡

በወጣው እጣ መሰረትም ድልድሉ የሚከተለውን ሆኗል፡-

ምድብ ሀ  

ሀዋሳ ከተማ ወላይታ ድቻ ኢትዮጵያ ቡና ፋሲል ከተማ 

ምድብ ለ 

ሲዳማ ቡና  አርባምንጭ ከተማ  ድሬዳዋ ከተማ  ወልዲያ 

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ  በውድድሩ ላይ የሚካፈል ዘጠነኛው ተሳታፊ የነበረ ቢሆንም የመስቀል በአልን በማስመልከት በአዲግራት በሚደረግ ውደድድር እንደሚካፈል በማሳወቅ ከውድድሩ ተገሏል፡፡

ነገ ውድድሩ ሲጀመር በ8:00 ሀዋሳ ከተማ ከፋሲል ከተማ የመክፈቻ ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡ በመቀጠል ደግሞ በ10:00 ወላይታ ድቻ ከኢትዮጵያ ቡና ይጫወታሉ፡፡ ዕሁድ እለት ከምድብ 2 አርባምንጭ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ በ8:00 ፤ ሲዳማ ቡና ከወልዲያ በ10:00 በሀዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *