​መስከረም ታደሰ የካፍ የሴቶች እግርኳስ ሲምፖዚየም አዘጋጅ ኮሚቴ ውስጥ ተካታለች

የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌድሬሽን (ካፍ) ዛሬ በአክራ ባደረገው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ሞሮኮ ላይ ለሚካሄደው የሴቶች እግርኳስ ሲምፖዚየም አዘጋጅ ኮሚቴ ውስጥ ኢትዮጵያዊቷ መስከረም ታደሰን መምረጡ ታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን ምክትል ዋና ፀሃፊ የሆነችው መስከረም ስድስት ሰዎችን የያዘው ኮሚቴ ውስጥ መካተት ችላለች፡፡

በመጋቢት 2018 በሞሮኮ የሚካሄደው የሴቶች እግርኳስ ሲምፖዚየም በአህጉሪቱ ሴቶች እግርኳስ ላይ የማሻሻያ ሃሳቦችን ያመጣል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በተለይ የሴቶች ክለቦች ውድድር የመጀመር ሃሳብ ለውይይት መቅረቡ የማይቀር ይመስላል፡፡ በኮሚቴው ውስጥ በቅርቡ በሙስና ተጠርጥራ ፍርድ ቤት በሚቀጥለው ወር የምትቀርበው የሴራ ሊዮን እግርኳስ ማህበር ፕሬዝደንት ኢሳ ጆንሰን፣ የፊፋ ካውንስል እና የካፍ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆነችው ሊዲያ ንስከራ እና የቀድሞ ሞሮኳዊት አትሌት ናዋል ኤል-ሙታዋክል ተካተዋል፡፡

መስከረም በሰቶች እግርኳስ ላይ በተለይ በኢትዮጵያ አበረታች ስራዎችን የሰራች ሲሆን የፊፋ ማስተር አልሙኒ ምሩቅ መሆኗንም ይታወቃል፡፡ መስከረም በ2017 ጋቦን ባስተናገደችው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ አስተባባሪ በመሆን ማገልገሏም ይታወሳል፡፡    

የኮሚቴው አባላት

ኢሳ ጆንሰን (ሴራ ሊዮን)

ሊዲያ ንስከራ (ብሩንዲ)

ናዋል ኤል-ሙታዋክል (ሞሮኮ)

መስከረም ታደሰ (ኢትዮጵያ)

ፓትሪሺያ ራጄሪሰን (ማዳጋስካር)

አልሃጅ አዬ ኦምዲራን (ናይጄሪያ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *