የፌዴሬሽኑ የኮከቦች ሽልማት ጥቅምት 12 ይካሄዳል

የፌዴሬሽኑ የኮከቦች ሽልማት ጥቅምት 12 ይካሄዳል
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሚያዘጋጀው የአመቱ ኮከብ ተጫዋቾች ምርጫ የሚካሄድበትን ቀን ለ3ኛ ገዜ ማራዘሙ እና ቀኑ ወደፊት እንደሚገለጽ ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡ አሁን ደግሞ ፌዴሬሽኑ ምርጫውን ጥቅምት 12 ቀን 2010 እንደሚያካሂድ ገልጿል፡፡

ፈዴሬሽኑ የሚያዳድራቸው ስድስቱ ሊጎች (ፕሪምየር ሊግ ፣ ከፍተኛ ሊግ ፣ አንደኛ ሊግ ፣ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ፣ ከ20 አመት በታች ፕሪምየር ሊግ እና ከ17 አመት በታች ፕሪምየር ሊግ) ኮከቦች በእለቱ የሚታወቁ ሲሆን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት እንደሚኖረውም ተገልጿል፡፡

የሽልማት ስነስርአቱ የት እንደሚካሄድ በይፋ ባይገለፅም የአፍሪካ ህብረት የመሰብሰብያ አዳራሽ ሊደረግ እንደሚችል ከፌዴሬሽኑ አካባቢ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *