ወልድያ ከሁለት ተጨዋቾቹ ጋር በስምምነት ተለያይቷል

የአዲስ የአሰልጣኝ ቅጥር በማድረግ በርካታ አዳዲስ ተጨዋቾችን ወደ ክለቡ የቀላቀለው ወልዲያ ሁለት ተጨዋቾችን በስምምነት መልቀቁ ታውቋል።

የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ምንያህል ይመር (ፎቶ ከላይ) በ2008 የዳሽን ቢራን መፍረስ ተከትሎ ወደ ወልድያ ያመራ ሲሆን በ2009 በርካታ ጨዋዋ ለቡድነ ማድረግ ችሏል፡፡ ተጫዋቹ የአንድ አመት ውል ቢቀረውም ከክለቡ ጋር ባደረገው ስምምነት ተለያይቶ ወደ ቀድሞ ክለቡ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በማምራት የ2 አመታት ኮንትራት ተፈራርሟል፡፡

የአጥቂ መስመር ተጨዋቹ በድሩ ኑርሁሴን ሌላው ውሉን በስምምነት አፍርሶ ወደ አማራ ውሃ ስራ ያመራ ተጫዋች ነው፡፡ የቀድሞው የሱሉልታ ከተማ አጥቂ በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከጫላ ድሪባ ጋር በመቀያየር የአንዷለም ንጉሴ አጣማሪ በመሆን ተጫውቷል፡፡


በአሰልጣኝ ዘማርያም የሚመሩት ወልዲያዎች የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ሀዋሳ ከተማ ላይ ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን ቡድኑ አሁን ወደ ወልድያ በመመለስ ዝግጅቱን ማከናወን እንደሚቀጥል ታውቋል።
ከክለቡ ጋር ባለመስማማት ልምምድ ያቆሙት አራቱ ተጨዋቾች ጉዳይ እስካሁን ምላሽ ያላገኘ ሲሆን ተጨዋቾቹ እስካሁን ድረስ ልምምድ አለመጀመራቸውን እና ከክለቡ ጋር መስማማት አለመቻላቸውን ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *