​ጅማ አባ ጅፋር ጋናዊ ግብ ጠባቂ አስፈርሟል

የፕሪምየር ሊጉ ክለብ ጅማ አባ ጅፋር ጋናዊው ግብ ጠባቂ ጃንኤል አጄይን አስፈርሟል፡፡ በዛሬው እለት ቡድኑ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው ጨዋታም ተሰልፏል፡፡

የ27 አመቱ አጄይ በሀገሩ ክለብ ሊበርቲ ፕሮፌሽናል እና ሚዲአማ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካው ፍሪ ስቴት ስታርስ የተጫወተ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቱ በፊት ለታንዛንያው ሲንባ ሲጫወት ቆይቷል፡፡ አጄይ በቅርብ አመታት ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ ተጫዋቾች የተሻለ ፕሮፋይል ያለውም ይመስላል፡፡ ለጋና ብሔራዊ ቡድን 22 ጨዋታዎች ላይ መሰለፍ የቻለ ሲሆን በ2010 የአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ በግብጽ ተሸንፎ ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው የጋና ብሔራዊ ቡድን አባል ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በ2009 የአፍሪካ እና የአለም ከ20 አመት በታች ቻምፒዮን የነበረው ቡድንም አባል ነበር፡፡

ጅማ አባ ጅፋር በስብስቡ ከአጄይ በተጨማሪ ማሊያዊው ተከላካይ አዳማ ሲሶኮን ከዚህ ቀደም ማስፈረሙ የሚታወስ ሲሆን ባለፈው አመት በወላይታ ድቻ ግማሽ የውድድር አመት ያሳለፈው ፍራኦል መንግስቱ እና ከወልዲያ ጋር በስምምነት ተለያይቶ ወደ አማራ ውሀ ስራ አምርቶ የነበረው በድሩ ኑርሁሴንም ክለቡን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *