የግብፁ ክለብ ኢ.ኤን.ፒ.ፒ.አይ የኢትዮጵያዊው አጥቂ ኡመድ ኡኩሪ ፈላጊ ክለብ መሆኑ ተነግሯል፡፡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የነበረው ውል ሰኔ 30 ላይ የተጠናቀቀው ኡመድ ወደ ኢ.ኤን.ፒ.ፒ.አይ ሊያመራ ይችላል፡፡ በግብፅ ፕሪሚየር ሊግ በሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ኢ.ኤን.ፒ.ፒ.አይ በ2016 በአፍሪካ ኮንፌድሬሽን ካፕ ተሳታፊ መሆኑ እና በገንዘብ አቅሙ ጠንካራ መሆኑ ኡመድን ወደ ክለቡ እንዲዛወር ምክንያት ሊሆን ይችላል ተብሏል፡፡ ኢ.ኤን.ፒ.ፒ.አይ ከኡመድ በተጨማሪ የሌላኛው ኢትዮጵያዊ የአጥቂ አማካይ ሽመልስ በቀለ ፈላጊ ክለብ ነው፡፡