​ቅዱስ ጊዮርጊስ ማሊያዊ አጥቂ አስፈርሟል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ማሊያዊው የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ሲዲ መሐመድ ኬይታን ማስፈረሙን በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ አስታወቋል፡፡

ኬይታ የሀገሩ ክለቦች በሆኑት ሲኦ ባማኮ እና ሲኤስኬ ያለፉትን 7 የውድድር ዘመናት ያሳለፈ ሲሆን በጁላይ 2017 የቱኒዚያ ሊግ 1 ክለብ ለሆነው ዩኤስ ቤን ጉኤርዳኔ ቢያመራም ጨዋታ ሳያደርግ ባልታወቀ ምክንያት ከክለቡ ጋር ተለያይቶ ወደ ኢትዮጵያው ቻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ በማምራት ከቀናት የሙከራ ጊዜዎች በኋላ በሁለት አመት ኮንትራት ተቀላቅሏል፡፡ እሁድ በአሸናፊዎች አሸናፊ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወላይታ ድቻን ሲገጥምም የመጀመርያ ጨዋታውን ሊያደርግ ይችላል ተብሏል፡፡

ዝውውሩ በቅዱስ ጊዮርጊስ የሚገኙ የውጭ  ተጫዋቾችን ቁጥር 4 ያደረሰ ሆኗል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *