​የእለቱ ዜናዎች | ረቡዕ ጥቅምት 22 ቀን 2010

ፕሪምየር ሊግ

የኢትዮዽያ ፕሪምየር ሊግ የ2010 የውድድር ዘመን በአራት ጨዋታዎች በይፋ የሚጀመር ይሆናል፡፡ በዚህ መሰረት:-

ቅዳሜ (25/02/2010)  

ጅማ አባጅፋር ከ ሀዋሳ ከነማ (ጅማ)

አርባምንጭ ከተማ ከ መቐለ ከተማ (አርባምንጭ)

ወልዲያ ከ አዳማ ከተማ (ወልዲያ)

እሁድ (26/02/2010)

ወልዋሎ አ/ዩ ከ ፋሲል ከተማ (አዲግራት)
የተቀሩት አራት ጨዋታዎች በቻን ማጣርያ ጨዋታ ምክንያት አዲስ አበባ ስታድየም ጨዋታ የማይደረግበት በመሆኑ ላልተታወቀ ጊዜ ተራዝሟል፡፡ ነገ ቀንና ሰአታቸው ይፋ እንደሚደረግም ሰምተናል።


ውሳኔ

ለአራት ወራት ውሳኔ ሳይሰጥበት የዘገየውና በሀዋሳ ከነማ እና በኢትዮ ኤሌትሪክ ጨዋታ መካከል ተፈጠረ በተባለው ጨዋታ ውጤት የማስቀየር ሙከራ ፈፅመዋል በማለት ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የዲሲፕሊን ኮሚቴ ነፃ ናቸው ሲል ወሰኗል።

ከጉዳዩ ጋር ስማቸው ይነሱ የነበሩት ዳዊት እስጢፋኖስ ፣ ፍፁም ገ/ማርያም ፣ ኤፍሬም ዘካርያስ ከተፈጠረው ውዝግብ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ጫና እንዳጋጠማቸው እየተገለፀ ሲሆን አሁን ውሳኔው ነፃ እንዲሆኑ ማረጋገጡ  ለተጨዋቾቹ እረፍት የሚሰጥ መልካም ዜና ሆኗል። ዲሲፕሊን ኮሚቴ ነፃ ናቸው ብሎ ለወሰነው ውሳኔ ባሳለፍነው ቀናት አቃቢ ህግ ተጨዋቾቹን በወንጀል ሊያስጠይቅ የሚያስችል ምንም አይነት ወንጀል አልፈፀሙም በማለት የወሰነው ውሳኔ እንደሆነ ታውቋል።  ሆኖም ውሳኔዎችን በፍጥነት ካለመወሰን ጋር ተያይዞ የኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከተደጋጋሚ ስህተቱ ሊታረም ይገባል ። ጅማ አባቡና ስፖርት ክለብ በተወሰነው ውሳኔ መሰረት የሚሰጠው መግለጫ ካለ በቀጣይ ይዘን የምንመለስ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።


ኢትዮጵያ ቡና

የኢትዮዽያ ቡና ዋና አሰልጣኝ መሆናቸው የተረጋገጠው አሰልጣኝ ኮስታዲን ፓፒች ዛሬ ለመጀመርያ ጊዜ ቡድኑ በልምምድ በሚሰራበት ሜዳ በመገኘት የቡድኑን እንቅስቃሴ በአካል በመገኘት የተመለከቱ ሲሆን አሁን መልስ ያላገኘው መልስ በአሰልጣኝ ገዛኸኝ ከተማ ምትክ ማን የኮስታዲን ረዳት እንደሚሆን ነው።


አክሊሉ አያናው

አክሊሉ አያናው ለፋሲል ከተማ እና ለኢትዮዽያ ቡና ፈርምሀል በሚል የዲሲፕሊን ኮሚቴ ተጫዋቹ ለፋሲል 600 ሺህ ብር እንዲከፍል ወስኖበት እንደ ነበረ ይታወቃል። ሆኖም አክሊሉ “እኔ ለፋሲል የፈረምኩት ሆቴል ውስጥ ነው፡፡ በመቀጠል መልቀቂያ አልሰጠሁም፡፡ ስለዚህ ለፋሲል ፈረመ ተብዬ የምቀጣበት ምንም የህግ አግባብ የለም” በማለት ለይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ቅሬታውን ያስገባ ሲሆን በመጀመርያ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ ፀድቋል፣ በመቀጠል 20ሺህ ብር እንዲከፍል ይደረግ የሚል ውሳኔ አሳልፎ ነበር። ዛሬ ደግሞ የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ በነፃ አሰናብቼዋለው ብሎ ለአክሊሉ ቢወስንም የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውሳኔውን እንዳገደው እየተነገረ ይገኛል። ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የወሰነውን ስራ አስፈፃሚ የሚያግድበት ምክንያት በየትኛው ህግ እንደሆነ ባይታወቅም የሚሆነውን ነገር በቅርብ ተከታትለን የምናቀርበው ይሆናል።


ጋዜጣዊ መግለጫ

የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ነገ 04:00 ላይ አምስት ኪሎ በሚገኘው የአአ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በሲቲ ካፑ ስለነበረው ሁኔታ ፣ በቀጣይ በጎደሉት የስራ አስፈፃሚ አባላት እና ጠቅላላ ጉባኤ ፣ ኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ስለ ሚያካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ተከትሎ አዲስ አበባ ስለወከለው እጩ እና ተያያዥነት ባላቸው ጉዳይ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥ ይሆናል።


ምርጫ 2010

ለቀጣይ አራት አመታት የኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በፕሬዝደንት እና በስራ አስፈፃሚነት የሚመሩ ተወካዮችን ለመለየት የፊታችን ጥቅምት 30 (ካልተቀየረ) ጠቅላላ ጉባኤው እንደሚካሄድ ይታወቃል። ምርጫውን ተከትሎ ክልሎች በየራሳቸው ከሚያደርጉት የዕጩዎችን ስም ከማሳወቅ ውጭ በአሁኑ ሰአት የእጩዎቹን ሙሉ ስም እስካሁን በይፋ ለጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊ አባላት እንዲሁም ለሚዲያው ሊያሳውቅ አልቻለም። በሌላ በኩል ደግሞ በአንዳንድ ክልሎች በኩል በተወካይ እጩዎች መካከል ውዝግብ እየተፈጠረ እንደሆነ ተሰምቷል። ምርጫው ሊደረግ የቀናት ጊዜ በቀረው በአሁኑ ሰአት እጩዎችን ፌዴሬሽን በይፋ አለማሳወቁ እያስገረመ ይገኛል።


ኦሮሚያ ዋንጫ

ያለፉትን አስር ቀናት በባቱ ከተማ አስተናጋጅነት በ6 የአንደኛ ሊግ እና የከፍተኛ ሊግ ቡድኖች መካከል ሲካሄድ የቆየው የኦሮሚያ ዋንጫ ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች ተጠናቋል፡፡ መቂ ከተማ ቡራዩ ከተማን 2-0 ሲያሸንፍ ቡልቡላ ሞጆ ከተማን 1-0 ረቷል፡፡ ዋንጫውን የማሸነፍ ሁለት እድል ይዞ የገባው አርሲ ነገሌ ከባቱ ከተማ 1-1 በሆነ የአቻ ውጤት ማጠናቀቁን ተከትሎ ባስመዘገበው አጠቃላይ በ11 ነጥብ የውድድሩ አሸናፊ በመሆን የዋንጫ ተሸላሚ መሆን ችሏል። ቡራዮ ከተማ በ10 ነጥብ አርሲ ነገልን ተከትሎ በ2ኛነት ሲያጠናቅቅ መቂ ከተማ በ10 ነጥብ በጎል ልዩነት አንሶ ሦስተኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡


ጥያቄ የሚያጭረው የተጫዋቾች ቅሬታ 

በተጫዋቾች እና በክለቦች መካከል የተፈፀመ ስምምነት አልተፈፀመም በሚል ምክንያት ተጫዋቾች በተደጋጋሚ ልምምድ እያቋረጡ ነው የሚለው ዜና እየተደጋገመ መጥቷል፡፡ ከቅሬታዎቹ ጀርባ ያለው ጉዳይ ግን አደናጋሪ ነው፡፡ ፌዴሬሽኑ ካወጣው የወርሀዊ ደሞዝ ህግ ባሻገር ስምምነታቸው ምን ነበር? አዳዲስ ፈራሚዎች “የተስማማነው ክፍያ አልተፈጸመልንም” ብለው ቅሬታ የሚያቀርቡት የአመት ክፍያቸው ቀድሞ እንዲከፈላቸው ስለሚስማሙ ነው? ይህ ጉዳይ ግልፅ አሰራር ካልተበጀለት አቅም በሌላቸው ክለቦች ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ ቀላል የማይባል ስለሚሆን እግር ኳሱን የሚመራው የበላይ አካል መፍትሄ ሊያስቀምጥለት ይገባል የብዙዎች ክለብ ጥያቄ ሆኗል።

ሌሎች ዜናዎች

ከታች ያሉት የዜና ርዕሶች አጠገብ Link የሚለውን በመጫን በዝርዝር ማንበብ ይችላሉ፡-

​ሳላዲን ሰዒድ በካፍ ኮከብ ሽልማት 30 እጩዎች ውስጥ ተካቷል – Link

​Salahdin Among the Nominees For African Player of the Year – Based in Africa – Link

​Salhadin nominé pour le meilleur joueur basé en Afrique – Link

​ብሔራዊ ቡድኑ 27 ተጫዋቾች ይዞ ነገ ልምምድ ይጀምራል – Link

​የደቡብ ካስቴል ዋንጫ ዛሬ የምድብ ጨዋታዎች ተጠናቀዋል – Link

​Ashenafi Names Squad as Waliyas Confirm CHAN Qualifier Participation – Link

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *