የ2007 ብሄራዊ ሊግ ውድድር ወደ መጨረሻው ምእራፍ ተሸጋግሯል፡፡ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ለማለፍ የሚደረገው ፉክክርም ሐምሌ 24 በድሬዳዋ አስተናጋጅነት ይጀመራል፡፡ በ8 ዞን ተከፍሎ ሲካሄድ በቆየው የዙር ውድድር ላይ ወደ ማጠቃለያው ውድድር ያለፉት ክለቦች የታወቁ ሲሆን ሀምሌ 23 በድሬዳዋ የምድብ ድልድል ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ከየዞናቸው ወደ ማጠቃለያው ውድድር ያለፉት ክለቦች የሚከተሉት ናቸው፡-
ምዕራብ ዞን ምድብ ሀ
1.ባቱ ከነማ
2.ሃላባ ከነማ
3.ሆሳእና ከነማ
ምዕራብ ዞን ምድብ ለ
1.ጅማ ከነማ
2.ጅማ አባቡና
-በዚህ ምድብ የሚወዳደሩ ክለቦች ቁጥር ዝቅተኛ በመሆናቸው 2 ቡድኖች ብቻ ወደ
ውድድሩ ያልፋሉ
ምስራቅ ዞን
1.ድሬዳዋ ከነማ
2.ሼር ኢትዮጵያ
3.ናሽናል ሲሚንቶ
ደቡብ ዞን
1.ደቡብ ፖሊስ
2.አርሲ ነገሌ
3.ሻሸመኔ ከነማ
ሰሜን ዞን ምድብ ሀ
1.ፋሲል ከነማ
2.አማራ ውሃ ስራ
3.ደ/ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
ሰሜን ዞን ምድብ ለ
1.መቐለ ከነማ
2.ወልዋሎ
3.ወሎ ኮምቦልቻ
ማእከላዊ ዞን ምድብ ሀ
1.ሱሉልታ ከነማ
2.ኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት
3.ፌዴራል ፖሊስ
ማእከላዊ ዞን ምድብ ለ
ኢትዮጵያ መድን
2.አ.አ. ከተማ አስተዳደር
3.ሰበታ ከነማ
4. ጥሩ አራተኛ – ቡራዩ ከነማ