ሲዳማ ቡና ዘላለም ታደለን ሲያስፈርም የረዳት አሰልጣኙ ጉዳይ አነጋግሯል

 

የይርጋለሙ ክለብ ሲዳማ ቡና የአርባምንጭ ከነማ አሰልጣኝ አለማየሁ አባይነህን የአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ረዳት አድርጎ መቅጠሩ እያነጋገረ መሆኑ ከክለቡ የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

አሰልጣኝ ዘላለም ከረዳት አሰልጣኙ ቾምቤ ገብረህይወት ጋር መስማማት ባለመቻላቸው ረዳታቸው እንዲሰናበቱ እንደሚፈልጉና አለማየሁ አባይነህ ወደ ክለቡ እንዲመጡ እንዳደረጉ ታውቋል፡፡ ክለቡም ለአለማየሁ 400ሺህ ወጪ አድርጎ ወደ ክለቡ ማምጣቱ ተወርቷል፡፡

ሲዳማ ቡና አለማየሁን በረዳት አሰልጣኝነት ቢቀጥርም አሰልጣኝ ቾምቤ እስካሁን አለመሰናበታቸው ታውቋል፡፡ በቀጣይ ቀናትም ከረዳት አሰልጣኝነታቸው ተነስተው ወደ ሴቶች ቡድን አሰልጣኝነት ሊሸጋሸጉ ይችላሉ የሚል ጭምጭምታም ተሰምቷል፡፡

ከክለቡ ጋር በተያያዘ ዜና ሲዳማ ቡና ተከላካዩ ዘላለም ታደለን ከወላይታ ድቻ አስፈርሟል፡፡ የወላይታ ድቻ አምበል የነበረው ዘላለም ክለቡን ለቆ አዳማ ከነማን የተቀላቀለው ሞገስ ታደሰን ቦታ ይሸፍናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሲዳማ ሌላውን የተከላካይ መስመር ተጫዋች አንተነህ ተስፋዬን ከአርባምንጭ ማስፈረሙ ይታወሳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *